፵፪ ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በተመረጡ አሥር የውይይት ነጥቦች ዙሪያ በቀደምት አበው ቅዱሳን ፓትርያርኮች ስም በተመደቡ አምስት ቡድኖች ማለትም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ፣በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት፣በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ስም በተመደቡ ቡድኖች ከዚህ በታች በተቀረጹ የውይይት ነጥቦች ማለትም፦
- የቤተክርስቲያን ፈተና መንስኤዎች ምንድናቸው?
- የቤተክርስቲያን ተግዳሮቶች ምንድናቸው?
- የውጭ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፤
- የአብያተ ክርስቲያናት ስደት ጉዳይ እንዴት ይደረግ?
- የቤተክርስቲያንን አንድነት እንዴት እናስጠብቅ?
- የሀገራዊ ምክክር ላይ የቤተክርስቲያን ድርሻ ምን መሆን አለበት?
- በቤተክርስቲያን ላይ የሚነሱ የሀሰት ትርክቶች ላይ ቤተክርስቲያን ምን ታድርግ?
- ግብረ ሙስናን በቤተክርስቲያን እንዴት አንታገለው?
- ሀገራዊ ሰላምን ለማስፈን የቤተክርስቲያን ድርሻ ምን ይሁን?
- ክብረ ክህነትን ለማስጠበቅ ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል?
በሚሉ ነጥቦች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ይገኛል:: በዚህ የቡድን ውይይት የሚነሱ ነጥቦች ተጨምቀው በምልዓት ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ማጠቃለያ ተሰጥቶባቸውና የተነሱት ነጥቦች በአቋም መግለጫው ተካተው ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚቀርቡ ይሆናል።