ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ “አሜን ኢትዮጵያ” የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ባተዘጋጀ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው የሰላም መልእክት አስተላለፉ ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን በሰበታ ጌተሴማኒ ገዳም በመገኘት የ፳፻ ፲ወ፭ዓ,ም የትንሣኤ በዓልን አከበሩ።

ቅዱስነታቸው በሰበታ ጌተሰማኒ ጠባባት ገዳም ከሚገኙ ሕጻናት ጋር የፋሲካን በዓል አከበሩ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን በሰበታ ጌተሴማኒ ገዳም በመገኘት የ፳፻ ፲ወ፭ዓ,ም የትንሣኤ በዓልን አከበሩ።

ከወደቅንበት የራስን ጥቅም የማሳደድ አዚም ወጥተን የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ሊያጸና የሚችለውን ሥራ እያስቀደምን ማገልገል የሁላችንም ውሳኔ መሆን እንዳለበት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ሚያዝያ ፱ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተካሄደው የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን ምክንያት የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ተካሔደ።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያና የየድርጅቶቹ የሥራ ኃላፊዎች ክቡር ሊቀ አእላፍ በላይ ጸጋዬ የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ፣የአድባራትና ገዳማት ከስተዳዳሪዎች እና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በቂም፣ በበቀል፣ በጥላቻ ወድቀን ትንሣኤውን እናከብራለን ማለት ትክክል እንዳልሆነ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተናገሩ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ብርሃነ ትንሣኤው የሰላም፣ የሕይወት፣ የጤና፣ የበረከትና የፍቅር ይሆን ዘንድ ተመኝተዋል፡፡

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እነሆ፤

የገብረ ሰላመ በዐል በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

የ፳፻ ፲ወ ፭ ዓ.ም የገብረ ሰላመ በዐል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት መ/ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያውና የየድርጅቶቹ ኃላፊዎች፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ጸጋዬ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ አምባሳደር ሬሚ Remi Marechaux በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሯል።

የሆሳዕና በዓል በተለያዩ አህጉረ ስብከት በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በድምቀት ተከበረ።

የሆሣዕና በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

በምስራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት በሱዳን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተከሰተውን አለመግባባት አጥንተው የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርቡ የሥራ ኃላፊዎች ካርቱም ገቡ።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ በሱዳን ካርቱም የሚገኘው መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳደርና በህዝበ ክርስቲያኑ መካከል የተከሰተውን አለመግባባት በማስመልከት በዝርዝር አጣርተው የውሳኔ ሀሳብ እንዲያቀርቡ የተመደቡት ሦስቱ የቤተክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎችና የአስተዳደር ጉባኤ አባላትም ሥራቸውን ለማከናወን ካርቱም ገብተዋል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በባሻ ወልዴ ችሎት የግንባታ ሥራው የተጠናቀቀውን ሕንጻ ቁልፍ ተረከቡ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኢኮኖሚ አቅሟን በተለያዩ የልማት ሥራዎች በማጎልበት ተቀዳሚ ተልዕኮዋ የሆነውን ስብከተወንጌልን ማስፋፋት፣የገጠር አብያተክርስቲያናትን የማጠናከር፣የአብነት ትምህርት ቤቶችን የማስፋፋትና የማጠናከር ሥራዋን ለማቀላጠፍ ያስችላት ዘንድ በተለምዶ ባሻ ወልዴ ችሎት በመባል በሚታወቀው ቦታ ላይ በአንድ ዓመት ውስጥ ያስገነባችው ዘመናዊ አፓርታማ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል።