ብፁዕ አቡነ አብርሃም በባህርዳር ሀገረ ስብከት ለአንድ ሺህ አምስት መቶ አገልጋዮች ክህነት ሰጡ።
የካቲት ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
የካቲት ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት በህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ድምቀት የተከበረውን የሐዋርያው የቅዱስ ቶማስ የሰማዕትነት መታሰቢያ በዓል በማስመለከት በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ከብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማር ቶማ ማቴዎስ ሦስተኛ የህንድ ማላንካራ ሲሪያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የክብር ጥሪ ተደርጎላቸው የነበረ ቢሆንም ቅዱስነታቸው በአካል ለመገኘት አስቀድሞ በተያዘ መርሐ ግብር ምክንያት ስላልቻሉ በቋሚ ሲኖዶስ በተወከሉ ልዑካን አማካኝነት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመረሻም ታላቅ ሀገር ይዘን፣ ምድሩ ሳይጠበን አመል እያጋፋን ነውና ጾማችን፣ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ ለሀገር ደኅንነት፣ ለሕዝብ ድኅነት እንዲያመጣልን እግዚአብሔር ይቅር ብሎን ዘመኑን በምሕረት ያሻግረን ዘንድ በታላቅ ንስሐ፣ በጸሎትና በአስተብቍዖት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ አባታዊ መልእክታችንን በመሐሪው አምላክ ስም እናስተላልፋለን።
የካቲት ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
****
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
“”””””””””””””””””””
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ይታወቃል፡፡
ሰኞ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራትን የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን እንዲሁም የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ እና በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም የተባሉት የገዳሙ የሥራ ሓላፊዎች እንደተገደሉ ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTCTV) በስልክ የገለጹት አንድ የገዳሙ የሥራ ኃላፊ በግፍ የተገደሉት አባቶች አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት በረሀማው ከጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ተፈጽሟል ብለዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊ ለጊዜው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለገዳሙ ጥበቃ እያደረገ ሲሆን ነገሮች እስኪረጋጉ ጥበቃው እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
© EOTC TV
የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
የካቲት ፲፪ ቀን ፲ወ፮ ዓ.ም
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የካቲት ፲፫/፳፻፲፮ ዓ/ም የዮርዳኖስ መንግሥት የቱሪዝምና የጥንታውያት ቅርሶች ሚንስትር ክቡር ማክራም ሙስጠፋ አብዱልከሪምን በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተቀብለው አነጋግረዋል።
የካቲት ፲፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
*******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን “መነኩሴ”በማስመሰልና በአርሲ ሀገረ ስብከት አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ የሚንቀሳቀሰውን ግለሰብ የማያውቀውና ሐሰተኛ “መነኩሴ” መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ።
ከየካቲት 12 ቀን 20916 ዓ.ም ጀምሮ በማኀበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ተችቶ የማስተቸት ድራማዊ ትዕይንት ላይ የቀረበው አስመሳይ ” መነኩሴ “ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በተለይ በአሰላ ከተማ በቅዳሴ መምህርነት በስብከተ ወንጌል እንዳገለ በማስመሰል በሰጠው የሀሰት ምስክርነትን በተመለከተ እውነተኛ ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ”መንኩሴ “መሳዩ ግለሱብ በሀገረ ስብከቱ በየተኛውም የከተማና የገጠር ገዳማትና አድባራት የማይታወቅና ምንም ዓይነት አገልግሎት ሲሰጥ ያልነበረ መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ሁሉንም አገልጋዮች የሚታወቁና የተመዘገቡ መሆኑን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ ግለሰቡ በሀገረ ስብከቱ ካሉት አገልጋች መካከል የማይታወቅና ያልተመዘገበ ከመሆኑም በላይ ሀገረ ስብከቱ በፍጹም የማያውቀው ቀሳጢ ነው በማለት ሐሰተኛ ማንነትን በመላበስ የቤተክርስቲያንን ስም ለማጠልሸተ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።
ስለሆነም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግለሰቡ የቤተ ክርስቲያናችንን ዓርማ ወይም አልባሳት በመልበስና የሀገረ ስብከታችንን መልካም ገጽታ በማጉደፉ ግለሰቡንና እዩ ጩፋ የተባለውን አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በህግ እንዲጠይቅን ስንል በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን፤በማለት ለጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ ጨምሮ ገልጿል።
ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት በሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል።
ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑም ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት ከሀገረ ስብከቱ በደረሰን መረጃ መሰረትም፦
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት
የካቲት 12 ቀን በታጣቂ ቡድኖች ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ታውቋል።
በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ መልካም ፈቃድ አሳሳቢነት የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩት አራት ደቀ መዛሙርት የዲቁና ሥልጣነ ክህነት በሰጡበት ወቅት ለአገልጋዮቹ በሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ትምህርት አስተምረው በዓለም ዙሪያ ያለችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በቅንነትና በእውቀት እንዲያገለግሏትም አባታዊ መመሪያም አስተላልፈዋል።