ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በአፋን ኦሮሞ የተተረጎሙ ሁለት መጽሐፍት ተመረቁ።

በዕለቱ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች፣ የወረዳ ቤተክህነት ሊቃነ ካህናት ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተክርቲያን ፣የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት፣ የማኀበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል አባላትና ዘማርያን እንዲሁም በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

የምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ከአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።

ሰኔ ፯ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም አዲስ አበባ

ከዓመት በላይ ያለ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ሥራቸውን ለመከወን ፈተና ውስጥ የቆዩት የምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ አባላት በግንቦት ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአባትነት ከተመደበላቸው ከብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ጋር በመገናኘት እና ገንቢ ውይይት በማድረግ የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
የአስተዳደር ጉባኤ አባላቱ ከብፁዕነታቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ያለ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ በቆዩባቸው ጊዜያት የሀገረ ስብከቱን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማሳለጥ ባለመቻላቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ መቆየታቸውንና ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ችግራቸውን ተመልክቶ አህጉረ ስብከቱን በፍጹም መንፈሳዊ የአባትነት መንፈስ ሊመሩ ሙሉ ፈቃደኝነቱ ያላቸውን ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልን በመመደቡ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የአስተዳደር ጉባኤ አባላቱ ከብፁዕነታቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ተዘግቶ የቆየውን የአህጉረ ስብከቱን የባንክ አካውንት በማስከፈት በውዝፍነት የቆየ የአገልጋዮችን ደመወዝ ለመክፈል ሥራ ከመጀመር ባለፈ በጅምር የቆሙ የልማትና የአስተዳደር ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል ዝግጁነታቸውን አሳይተዋል።
ብፁዕነታቸው ለአስተዳደር ጉባኤ አባላቱ በሰጡት አባታዊ መመሪያም ጠንክረው በመሥራት ቤተ ክርስቲያናችን በዞኖቹ ያላትን በጎ ስም አስጠብቀው ለትውልድ እንዲያስተላልፉ አሳውቀዋል።

ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር ቅዱስ ሲኖስ ያወጣውን የማኅበራት ምዝገባ መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጠው።

ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.

የገዳማት አበ ምኔቶች እና እመ ምኔቶች በቤ ተክርስቲያችን ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፡፡

ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ

የኢኦቴቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት የቀጥታ የሳተላይት ቴሌቪዥን ሥርጭት ለመጀመር ባከናወነው ተግባር ለተሳተፉ አካላት የምስጋና ፕሮግራም እያካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የሰሜንና ምሥራቅ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ በችግር ሰዓት የቆመ ጣቢያ መሆኑን ጠቅሰው በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ደብዳቤ መነሻነት ለተራዱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ሌሎች አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የ፳፻ ፲፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማጠቃለያ መግለጫ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡