የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር ቅዱስ ሲኖስ ያወጣውን የማኅበራት ምዝገባ መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጠው።

June 12, 2024

ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
==============
ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር ለሚገኙ ማኅበራት ሕጋዊ ሰውነት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ያጸደቀውን ደንብና መመሪያ አሟልቶ በመገኘቱና ለአንድ ዓመት ያህል በማኅበሩ ዙሪያ በተደረገው ጥናት ማኅበሩ ዕውቅና ቢሰጠው በቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት የራሱን በጎ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ስለታመነበት የዕውቅና ምስክር ወረቀቱን ሊያገኝ እንደቻለ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨው፣ የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት እና በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ  እና   የማኅበራት ማደራጃ፣ ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ ሊቀ ጳጳስ በዕለቱ ገለጹ።

በዚሁ ጊዜ የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር  ቅድስት  ቤተክርስቲያንን  ለማገልገል  ከፍተኛ  ኃላፊነት  እንደተጣለበት  የገለጹት ብፁዕነታቸው ማኅበሩ የቤተክርስቲያናችንን  ዶግማ፣ ቀኖና፣  ሥርዓት  እና  ትውፊትን ጠብቆ ሊሠራ  እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

ብፁዕነታቸው አክለውም የማኅበራት ማደራጃ፣ ምዝገባና  ቁጥጥር መምሪያ  ባለፉት  ወራት  ለ12 መንፈሳውያን ማኅበራት እውቅና  መሰጠቱን  ገልጸው የዕውቅና የምስክር ወረቀቱም ለሦስት  ዓመታት  ብቻ  የሚያገለግል መሆኑን ጠቁመው ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበርን  ጨምሮ  ሌሎች  መንፈሳውያን  ማኅበራት  ከቅድስት  ቤተ ክርስቲያን  ሥርዓት  ውጪ የሆኑ ተግባራትን ፈጽመው  ከተገኙ የተሰጣቸው የዕውቅና ምስክር ወረቀት
እንደሚሰረዝም  ገልጸዋል፡፡

የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ መጋቤ አእላፍ  ጸጋዬ ደበበ  በበኩላቸው  ለማኅበሩ የዕውቅና የምስክር ወረቀት መሰጠቱ  እንዳስደሰታቸው  በመግለጽ   ቤተክርስቲያን  የጣለችባቸውን  ኃላፊነት  ለመወጣት  ኦርቶዶክሳዊያን  ከጎናቸው እንዲቆሙ  ጥሪያቸውን  አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም  መንፈሳዊ  ማኅበሩ  በቀጣይ ከሚያከናውናቸው መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ልማታዊ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ ደረጃውን  የጠበቀ  የሚዲያ ተቋም ለመገንባት እና  ቅድስት  ቤተክርስቲያንን  የሚጠቅሙ  ሌሎች  ዘርፈ  ብዙ  ተግባራትን  ለማከናወን  ማቀዱን  መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ጨምረው ገልጸዋል።

መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ባለፈው ወር ከማኅበሩ መዝሙራትና የመዝሙር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ውዝግብ በማስመልከት በመገናኛ ብዙሃን በይፋ ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።

ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና ከማግኘቱ በፊት በመንፈሳዊ፣
በማኅበራዊና ልማታዊ  ተግባራት ዙሪያ በመሰማራት ገዳማትን በመርዳት፣ አዳዲስ የሚተከሉና እድሳት የሚደረግላቸውን አብያተ ክርስቲያናት ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ በመገንባት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመደጎምና በማገዝ፣ የካህናት ማሰልጠኛዎችንና መንፈሳዊ ኮሌጅችን በጀት መድቦ ጭምር በመደገፍና በቤተ ክርስቲያናችን የሚደረጉ ተቋማዊ ሥልጠናዎችን ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈንና የቤተ ክርሰቲያናችን የሚዲያ ተቋማትን ስቱዲዮ በመገንባት መንፈሳዊ ግዴታውን በብቃት የተወጣና በመወጣት ላይ የሚገኝ ማኅበር ነው።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የገዳማት አበ ምኔቶች እና እመ ምኔቶች በቤ ተክርስቲያችን ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፡፡ Link to: የገዳማት አበ ምኔቶች እና እመ ምኔቶች በቤ ተክርስቲያችን ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፡፡ የገዳማት አበ ምኔቶች እና እመ ምኔቶች በቤ ተክርስቲያችን... Link to: የምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ከአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሥራ መመሪያ ተቀበሉ። Link to: የምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ከአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሥራ መመሪያ ተቀበሉ። የምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት የአስተዳደር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top