በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተመራ የመስቀልና ደመራን በዓል አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመንበረ ጵጵስና አዳራሽ ስብሰባ ተካሄደ።

መስከረም ፬/፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

ሰንበት ት/ቤቶች ከመዘመር ባሻገር መሠረተ ሃይማኖት ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ)

መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም

በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በደብረ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ  በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

መስከረም 2/2017 ዓ/ም

የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ዕረፍቱ በወናጎ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ክብርና ድምቀት ተከበረ !!!

መስከረም 2/2017 ዓ.ም

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር አካሄደ።

መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም.

በከሚሴ ሀገረ ስብከት የከሚሴ ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤል ሰበካ ጉባኤ የ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመትን እና የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን መታሰቢያ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምህረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም(በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል) መዝ 65:-11

ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳቸው መልእክት አስተላለፉ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ
ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም፤

በቸርነትህን ዓመታትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል” መዝ. ፷፬፡፲፩

በሀገራችን በኢትዮጵያ እንዲሁም በተለያዩ ዓለማት የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን አባቶች፣እናቶች፣ወንድሞትችና እህቶች ሕጻናት የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፣

  • በየሆስፒታሉ
  • በየማረሚያ ቤቱ
  • በጸበል ቦታው በተለያዩ ቦታ የምትገኙ ወገኖች በሙሉ

ከሁሉ አስቀድሞ ልዐል እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ሆኖ በመለኮታዊ ጥበቃው ጠብቆ ይህነው ተብሎ በማይመረመረው አምላካዊ ፍቅሩ ጠብቆ ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ ስላሸጋገረን ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን እያልኩ ዘመነ ማቴዎስ የሰላም የጤና የሕይወት የበረከት የዕድገት ዘመን ይሆንላችሁ ዘንድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲሁም በባሕርዳርና በሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ስም እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።

ቸርነትና ምሕረት የባሕርይው ገንዘቡ የሆኑለት አምላካችን እግዚአብሔር ወሰን በሌለው አባታዊ ፍቅሩና መግቦቱ ሳይለየን ጠብቆና አቆይቶ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ ከ2016 ወደ 2017 በድጋሜ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ።
የዐዲሱ ዓመት የሰላምና የአንድነት የሥራና የመግባት የፍቅር ዓመት ይሁልን።

ቀደም ብየ በጠቀስኩት የመዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት ቃል በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ። ይህን ዓመት የተቀበልነው በእግዚአብሔር ቸርነት ነው በሥራችን አይደለም። ሥራችን በእግዚአብሔር ፊት ቢመዘን ምንም የሚያስከፍል ዋጋ አይኖረውም። ምክንያቱም በብዙና ብዙ ነገሮች እንቅፋትና ውጣ ውረዶች የበዙበት የተሰነካከለ ሕይወት ሊኖረን ስለሚችል እግዚአብሔር ግን ቸር ስለሆነ በየጊዜው በልዩ ጥበቃው እየጠበቀ ዓመትን ያቀዳጃናል። ዓመትን ባቀዳጀን፣ ዘመንን በጨመረልን፣ ተጨማሪ ዕድሜ በሰጠን ቁጥር ግን ከእኛ የሚጠበቅ ነገር አለ።

እኛ የሰው ልጆች የዘራውን እንዲያፈራ ያሰብነው እንዲሳካ ጥረት እንደምናደርግ ሁሉ ጥረታችን ባይሳካ ደግሞ ኀዘን ከፍ እንደሚል ሁሉ ለምስጋና የፈጠረን ከልዩ ልዩ ፍጥረታት ሁሉ ከፍ አድርጎ የፈጠረን እግዚአብሔር ደግሞ ከእኛ ተነሣሒነትን ይፈልጋል። ፍቅርን ይፈልጋል ሰላምን ይፈልጋል። የሰጠን ዘመን ክፋት ልንሠራበት አይደለም ተንኮል ልንፈጽምበት አይደለም ግፍ ልንፈጽምበት አይደለም በርኅራኄ በፍቅር በአንድነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ሥራ ልንሠራበት የተሰጠን ዘመን ነውና የተቀዳጀነውን ዘመን እንጠቀምበት።

ይህ ዐዲሰሰ ዓመት ሁልጊዜም ቢሆን የተመረጠ ዕለት የተመረጠ ዓመት እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ኢሳይያስ በትንቢቱ በኋላም በሐዲስ ኪዳን ቅዱስ ሉቃስ መዝግበውልናል ።

“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል” ሲል አረጋግጦሎናል።ሉቃስ ፬፥፲፯

ስለዚህ ይህ የተወደደ ዓመት ይህ ተጨማሪ በልዩ ስጦታ በፈቃደ እግዚአብሔር የተሰጠን ዓመት ዝም ብሎ በከንቱ የተሰጠን አለመሆኑን መረዳት አለብን። ስለሆነም ለድሆቾ የምስራች የምንሠብክበት የምሥራችን ለትንሹም ለትልቁም የምንነግርበት ነው። ድሆች ስንል የቁሳቁስ ድኅነት ያላቸውን ብቻ አይደለም በተለምዶ ድሀ ብለን የምንጠራው ቁሳቁስ የሌለውን የወደደውን ለመሥራት ያሰበውን ለመግዛት የማይችለውን ሊሆን ይችላል። ይልቁንም ቁሳቁሱ ኑሮም የበለጠ ድህነት ስለሚኖር ስለዚህ ከማንኛውም ድህነት ከሚል ቋንቋ ከመንፈስም ከሥጋ ነጻ ለመሆን ተግቶ መሥራት እንደመንፈሳዊ መንፈሳዊ ሥራ እንደ ሥጋዊ ሥጋዊውን ሥራ ለሕይወት ተስማሚ የሆነውን ሰውንና እግዚአብሔርን የማያሳዝነውን ሥራ በመሥራት የምሥራች ተናጋሪዎች እንድነሆን ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል።

ለታሰሩትም መፈታትን ማሳሰር ሳይሆን ማስፈታት። ብዙ ጊዜ በግፍ፣ በሐሰት በቅንብር እንዲታሠሩ የሚያደርግ ይታያዩ ይሰማሉ። እንደቅዱስ መጽሐፍ ደግሞ የታሰሩትን ማስፈታት እንጂ ባልዋሉበት ምን ይሄ ነው ተብሎ ወንጀላቸው ባልተረጋገጠበት የሚደረግ ማሳሰር ሁሉ ተገቢ አይደለም። ስለዚህ በአዲሱ ዓመት የታሠሩ በይቅርታ በምሕረት የሚፈቱበት ወንጀል ቢሠሩም ይቅርታ በትልቅ አስተማሪ ስለሆነ ምሕረት ማድረግ በእግዚአብሔርም በሰው ዘንድ የተወደደ ነውና። የራቁ የሚቀርቡበት ፍቅርና ሰላም የሚሰበክበት እንዲሆን እግዚአብሔር ይርዳን እላለሁ።

ለዕውራንም ማየትን ዐይን እያላቸው ማየት የተሳናቸው ብልጭልጩን ዓለም እንጂ መንፈሳዊውን ዓለም ማየት ዕድሉ የተነፈጋቸው ከዚህ ድርግም ብልጭ ከሚለው ብልጭልጩ ዓለም ይልቅ ዘለዓለማዊ ብርሃን የሰፈነበትን ከከበሩ የማይደሀዩበትን ካገኙ የማያጡበትን ከተሾሙ የማይሻሩበትን የእግዚአብሔርን መንግሥት ወርሶ ለመኖር የሚያስችለውን ዕይታ ያዩ ዘንድ ሁላችንም የምስራች ተናጋሪና የ
ነጻነት አብሣሪ ሰላምን የምናወጅ እንደንሆን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ነው።

የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ ይላል በልዩ ልዩ የተጠቁ ወገን ያጡ በሐሰት በቅንብር ፈተና ላይ የወደቁትን እውነታውን አውጥቶ ምክንያቱም ከሰው የሠወረና ሰው የማያውቀው ነገር ስለሌለ እንደጎረቤትም በቅርብም በሩቅም ያለምን ኃጢአታቸው የተጠቁ ወገኖች ካሉ አግባብ አይደለም እግዚአብሔርን ያሳዝናል የንጹሐን ግፍ ደግሞ በሀገርም ላይ በወገንም ላይ ሌላ ፈተና ያመጣልና ነጻ ይውጡ ብሎ በምክክር በውይይት ፍቅርና ሰላምን አሁንም የምሥራች ብሎ በመናገር ልንሠራ የሚገባንን እንድንሠራ የእግዚአብሐር ቃል ነው።

ቀጥሎም የተወደደችውን የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ይላል ቃሉ። ይህች ዓመት የተወደደች የጌታ ዓመት ናት። የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዓመት ልዩ ሥጦታ ናት። ዓመተ ምሕረት ስንል ምንጊዜም ቢሆን የምናስታውሰው ከጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ወዲህ ነው በብሉይ ኪዳን የነበረው ዘመን ዓመተ ኩነኔ ዓመተ ፍዳ የስቃይ የመከራ ዓመት ተብሎ ነው የሚጠራው ምንክያቱም ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበሩት የዓመታት የጨለማው ዘመን የፍዳ ዘመን ተብሎ ነው የሚጠራው። ክርስቶስ ከመጣ በኋላ ግን የታሠሩትን በማስፈታት፣ ዕውራንን እንዲያዩ በማድረግ የራቁትን በማቅረብ የተጠቁትን ነጻነት በመስጠት የተዋረዱትን ከፍከፍ በማድረግ የተሠራበት ስለሆነ ዓመተ ምሕረት የተጀመረበት ነው።

ስለዚህ ዛሬ ለእኛ የተጨመረን ይህ የተወደደ ዓመት ዘመነ ማቴዎስ ባለፈው ዓመት በማወቅም ይሁን ባለማማወቅ፣ በድፍረትም ይሁን በስህተት፣ በመሰለኝም ይሁን በግዴለሽነት፣ ከእግዚአብሔር የራቀ የሕሊና ጸጸት የሚያስከትል የሠራነው ሥራ እስካለ ድረስ በጸጸት የእግዚአብሔር መሐሪነቱን በማመን በዚህ በያዝነው አዲስ ዓመት በትክክል በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተወደደውን ለሕሊናም ጸጸት የለሽ ሥራ ለመሥራት ቆርጦ መነሳት የሁላችንም ድርሻ ነው። ስለሆነም የንስሐ ጊዜ ዛሬ ነው ነገ አይደለምነመ ጊዜው ሳይመሽ በተሰጠን ዘመን ንስሐ በመግባት ልንጠቀምበት ይገባል።

እግዚአብሔር ጊዜ የሚሰጠው እኛ የእሱ ልጆች እንድንሆነንና ሆነን እንድንኖር ነው። በዚህ ዘመን እንደ ሀገር ሰላም ያጣቸው ሀገራችን ሰላም የምትሆንበትን እንደ ቅድስቶ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ስሟም ክብሯም ዝቅ ብሏልና ከፍ የሚልበት፤ አዲስ እንፍጠር አዲስ ሥርዓትም እናምጣ አ ማለታችን አይደለም። የነበረው ሥርዓታችን በካህኑ ታማኝነት የማይታጣበት፣ በእጁ ምንም የማይሟሟበት አባቶቻቸን በአባባል “ቅቤ እጁ ላይ ሆኖ የማይሟሟበት” እንደሚሉህ ቀደምት አባቶቻቸችን እንደዚህ ናቸው።እነሱ እየተራቡ ሌላውን በታማኝነት የሚያጠግቡ፣ እነሱ እየተጠሙ ሌላውን ከችግር እንዲላቀቅ የሚያደርጉ፣ ለሃይማኖታቸው ወለም ዘለመ የማይሉ ጽንዓን ፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንክብር ጠባቂዎች ፤ የሀገረ ፍቅር የወገን ፍቅር ነበራቸው ለወገን የሚሳሱ ነበሩ።

ዛሬ ግን ራስ ወዳድነቱ ሠልጥኗልና እግዚአብሔር ከሰጠን ክብር ይልቅ የቁሳቁስ ፍቅርና ክብር ሰልጦኗልና እንዲህ ዓይነቱን ግብር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቃ ብለን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም የምንዘጋጅበት ጊዜ እንዲሆን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም መልእክቴን አስተላልፋለሁ።

በመጨረሻም እነሆ ይህ ዓመት እንደቅድስት ቤተ ክርስቲያን በልማት በፍቅር የተቸገሩትን በመርዳት የተጣሉትን በማስታረቅ የተፈናቀሉትን ወደ ሥራቸው በመመለስ በተለይ አብያተ ክርስቲያናት አህጉረ ስብከት በተለያየ ቦታ ተፈናቅለናል ተቸግረናል ብለው በየዐደባባዩ የሚያለቅሱ አሉና እነሱንም ወደ ሥራቸው በመመለስ፣ ዕንባቸውን በማበስና ችግራቸውን በማራቅ ሁልጊዜም ደስ ብሏቸው እንዲኖሩ በእናታቸው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቤታቸው ላይ እንዲኖሩ ልንሠራው የሚገባን እንድንሠራ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስም አሳስባለሁ።

ቤቱ የሁላችንም ነው። ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጅ የእንጀራ ልጅ የሚባል የላትም የሥራ ድርሻ ይለያይ እንጂ ሁላችንም ልጆቿ ነን። ስለሆነም አንዱ ገፊ አንዱ ተገፊ፤ አንዱ አቅራቢ ሌላው ቀራቢ የሚሆንበት መንገድ በኋላ የሚያመጣው ፍዳና ፈተና ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ነውና በምንም ይሁን በምንም አይመከርም። አይሞከርም።

ስለዚህ ሰው እስከሚፈርድብን ድረስ መራመዱ፣ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ መቀመጡ እጅግ አደገኛ ነውና በዚህ ሰምቶ ሰምቶ እግዚአብሔርም ስለሚፈርድ እነሆ ልባችን ተሰብሮ በንስሐ ተመልሶ፣ ከልህ ወጥተን፣ከእግዚአብሔርን ሥራ ሠርተን፣ በፊቱ ሞገስ አግኝተን ዘመነ ማቴዎስ ከኃጢአት የምንርቅበት ከግፍ ከበደል ርቆ ሁሉም ፈቃደ እግዚአብሔርን የሚፈጽምበት ፤ ሀገራዊ ፍቅሩን የሚያሳይበት፣ ያጣነው ሰላም የሚያገኝበት ይሆን ዘንድ ቸርነቱ አይለየን። አዲሱ ዓመት የሰላም የአንድነት የሥራ የመግባባትና የፍቅር ዓመት ይሁንልን ።

በዓሉን ስናከብር የተራበውን በመመገብ የተጠማውን በማጠጣት፣ የተቸገረውን በመርዳት፣ ታመው በየሆስፒታሉ ያሉትን እግዚአብሔር ይማራችሁ ብሎ በመጎብኘት፣ እንዲሁም በየማረሚያ ቤቱ እግዚአብሔር ያስፈታችሁ በማለት በዓሉን እንድናከብረው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪ ነው።

እግዚአብሔር አምላካችን ወዶና ፈቅዶ ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ዘመነ ማቴዎስን ስለሰጠን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁንልን።

ዘመናችን እግዚአብሔር ይባርክልን።
መልካም አዲስ ዓመት

አባ አብርሃም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መስከረም ፩/፳፻፲፯ ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የመጥምቀ ክርስቶስ ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሯል (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት)

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በበዓሉ ለተገኙ ምእመናን ዕለቱን አስመልክተው ትምህርትና ቃለ ምእዳን አስተላልፈዋል።

በዲላ ጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የቅዱስ ሩጉኤል ክብረ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ክብርና ድምቀት  ተከበረ።

መስከረም 1/2017 ዓ.ም

በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ራጉኤል በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

መስከረም 1/2017 ዓ/ም