የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ክብር በዲላ ከተማ ተከበረ!!

September 27, 2024

መስከረም 16/2017 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከበረ ።
በዕለቱም የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የርቀትና ኦን ላይን ኮሌጅ ዲን ሊቀ ህሩያን አባ ገ/ሐና ፣የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ብርሃኑ ክፍሌ ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች ፣የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ፣ የዲላ ከተማ ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሽፈራው፣ የጌዴኦ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባየሁ ኢሳይያስ፣ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን የዲላ ከተማና አካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ተገኝተዋል።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ያደረገልንን የማዳን ሥራ መስበክ ለክርስቲያኖች ቀዳሚ ተግባር መሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ክቡር መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በሚከበረው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ አስተላልፈዋል።

ክቡር ሥራ አስኪያጁ በመግለጫቸው “የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው” ብሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ መልእክቱ የጻፈውን በመጥቀስ እኛ ክርስቲያኖች ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ያደረገልንን የማዳን ሥራ መስበክ ለእኛ ክርስቲያኖች ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል።

በመጨረሻም ለበዓሉ መሳካት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን የመንግሥት አካላት የፖሊስ ኃይሎችን ፣ የሃገረ ስብከቱን የየክፍል ሃላፊዎችን ፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ሰራተኞችን ፣ የየአድባራቱን አስተዳዳሪዎች ፣ ካህናቱን እንዲሁም በበዓሉ የተገኙ ምዕመናንን በማመስገን መግለጫቸውን አጠናቀዋል።

የዕለቱን ትምህርትና ያስተማሩትና መልዕክት ያስተላለፉት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የርቀትና ኦን ላይን ኮሌጅ ዲን ሊቀ ህሩያን አባ ገ/ሐና ሲሆኑ ለሚፈሩኸ ምልክትን ሰጠኻቸው በማለት ስለ ቅዱስ መስቀል ክብር በሰፊው አስተምረዋል።

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ለዘመናት ታሪክን ቅርስን የጠበቀች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሆኗን ገልጸዋል።
የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሽፈራው በመልዕክታቸው የመስቀልን ክብር አንስተው የደመራን ትርጉም በመዘርዘር ይኸን የቅዱስ መስቀል በዓልን ማክበራችን በህላዊና መንፈሳዊ ዕሴታችንን ማስቀጠል ይገባናል በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትን አስተላልፈዋል።

በበዓሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና የሰንበት ት/ቤት አንድነት ያሬዳዊ ወረብን አቅርበዋል። በሊቀ ህሩያን አባ ገ/ሐና ቡራኬና ጸሎት ተደርጎ በሀገረ ስብከቱ ሥራአስኪያጅ በመልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ እና በክቡር የዞኑ አስተዳደር የጋራ የደመራ መለኮስ ሥነ ሥርዓት ተከናውኖ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የከሚሴ ሀገረ ስብከት መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ከተማ የመስቀል በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የከሚሴ ሀገረ ስብከት መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ከተማ የመስቀል በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን... Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በድምቀት ከሚከበሩት የአደባባይ በዓላት አንዱ የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሃይማኖታዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከበረ። Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በድምቀት ከሚከበሩት የአደባባይ በዓላት አንዱ የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሃይማኖታዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከበረ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top