የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን የጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑ እናበስራለን፡፡
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት፤

ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ሥር የተቋቋመው የሕግ ባለ ሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ አካሔደ።

ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም.

ኹለተኛው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የ12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ ተከናወነ።

ጥቅምት 2 ቀን 2017ዓ.ም.

ለሦስት ወራት በ6 አህጉረ ስብከት ሲካሄድ የነበረው ሐዋርያዊ ጉዞ ለቤተክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ትርፎችን በማትረፍ ተጠናቀቀ

ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም.
+ + +

የጋምቤላ ፣ የቄለም ወለጋ፣ የአሶሳ፣ የምዕራብ ወለጋ ፣ የሆሮ ጉድሩ ፣ የምስራቅ ወለጋ እና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ የጋምቤላ ክልል እና የቤኒ ሻንጉል ክልል የሰላምና የልማት አንባሳደር ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ከሐምሌ 2016ዓ.ም. ጀምሮ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በህገ ወጡ ሹመት ምክንያት ወደ ሕግ ያልገቡ አህጉረ ስብከቶችን ወደ ሕግ ከማስገባት ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ቱሩፋቶችን ለቤተክርስቲያን በማትረፍ ሐዋርያው ጉዟቸውን ማጠናቀቃቸውን የምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብክት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ።

ብፁዕነታቸው በሁሉም አህጉረ ስብከት የቤተክርስቲያንን አንድነት በማስጠበቅና ሥርዓትን በመዘርጋት ዘርፈ ብዙ ውጤት ያሳዩ ሲሆን ከጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ሕገ ወጥ ሹመት በኋላ ከሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊነት ተለይተው የነበሩት የሦስቱ ወለጋ አህጉረ ስብከት በዘንድሮው ዓመት በሚከበረው 43ኛው የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ከየሀገረ ስብከቱ ሰባት ሰባት ልዑካን ተወክለው ወደ መንበረ ፓትርያርክ እየመጡ እንደሆነ ተገልጿል።

የ7ቱ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሐዋርያዊ ጉዟቸው ማጠናቀቂያ ላይ በጊንቢ ከተማ በአቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ጸሎተ ኪዳነ አድርሰው የጉዟቸው መጀመሪያ አድረገውት ወደነበረው ምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት በማቅናት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅና የየክፍል ኀላፊዎች፣ የሆሮ ጉድሩ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አሥኪያጅና የየክፍል ኀላፊዎች በነቀምቴ ከተማ የሚገኙ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ሊቃውነተ ቤተክርስቲያን እና የሰንበት ትምርት ቤት ወጣቶች በተገኙበት ህገ ቤተክርስቲያንን ጠብቆ በማስጠበቅ ረገድ መመሪያ ሰጥተዋል።

በ42ኛው የሰባካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ያልበሩት ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩና ምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት ወደ እናት መንበራቸው በመመለስ ከጥቅምት 4-10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚከበረውን 43ኛው የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የበጀት ዓመቱን ቅጽ በመሙላት ከብፁዕነታቸው ጋር በመሆን ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀምረዋል።

ብፁዕነታቸውና የሀገረ ስብከቱ ልዑካን ወደ መንበረ ፓትርያርክ ሲያቀኑ በነቀምቴ ከተማ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ ካህናት ፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና ምዕመናን ሽኝት አድርገውላቸዋል።

ዘገባውን ያደረሰን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

በህገ ወጥ መንገድ ተሠብሮ ከአገልግሎት ውጪ የነበረው  የምዕራብ ወለጋ መንበረ ጵጵስና   ጥገና ተደገርጎለት  በሰባቱ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተባርኮ  ዳግም አገልግሎት  መስጠት ጀመረ።

መስከረም 29 ቀን 2016ዓ.ም.

ኮሚቴው የማጣራት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ለጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ሪፖርት አቀረበ።

መስከረም ፳፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው በአዲስ አበባ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጋር በሀገረ ስብከቱ በሚከናወኑ ዕቅዶች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

መስከረም 27 ቀን 2017ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበራት ምዝገባ፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ፈቃድ ከተሰጣቸው ማኅበራት ጋር የምክክርና የውይይት መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው።

መስከረም 27 ቀን 2017ዓ.ም.