የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

October 31, 2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ስለምጣኔ ሀብት እድገት፣ በሀገራችን እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን
አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-

1. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

2. በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡

3. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

4. የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆነ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ
ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

5. የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣

6. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኀበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ Link to: መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ Link to: እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ Link to: እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top