መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””””””””
ጋምቤላ-ኢትዮጵያ
****
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላና የደቡብ ሱዳን፣ የቤኒሻንጉል አሶሳ፣ቄለም ወለጋ ቤጊ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጋምቤላ ሀገረስብከት መጃንግ ዞን መንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች ለሐዋርያዊ አገልግሎት በመጓዝ ሦስት አዳዲስ የተሰሩ አብያተክርስቲያናትን በመባረክ ቅዳሴ ቤታቸውን አክብረዋል።

በመቀጠልም የጸጥታ ችግር በሚስተዋልባቸው ዱሺና ጉበቲ በተባሉ ሥፍራዎች በመጓዝም በአካባቢው የሚገኙ ምዕመናንን በማጽናናትና ትምህርት በመስጠት ነዋሪዎችን አረጋግተዋል። በቢሻን ዋዮ ሀይቅ ላይ የቅድስት አርሴማ ገዳምን ለመገደም የመሰረት ድንጋይ አኑረዋል።በዐቢይ ሦስት ላይም የመንበረ ጵጵስና ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አኑረዋል።

ብፁዕነታቸው በጎደሬ ሜጢ ጌቴሴማኒ እየተገነባ ያለለውን G+3 የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታም ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ የሃምሳ ሺህ ብርና የላፕቶፕ ድጋፍ አድርገዋል።በጎደሬና በመንገሺ አካባቢ ለሚገኙ ካህናት፣ዲያቆናትና የሰበካ ጉባኤ አባላትም በቃለ ዐዋዲና በሕገ ቤተክርስቲያን ዙሪያ የአንድ ቀን ሥልጠና ሰጥተዋል።ቀጣዮን ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውንም ደቡብ ሱዳን ጠረፍ በሚገኘው ዲማ በረሃ ለማከናወን ወደ ሥፍራው ማምራታቸውን በመግለጽ ዘገባውን ያደረሰን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።