ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጥቅምት ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ምልአተ ጉባኤውን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የመክፈቻ መልዕክት ዛሬ ጠዋት መጀመሩ ይታወቃል ።
ከቅዱስነታቸው የመክፈቻ መልእክት በኋላም የመወያያ አጀንዳ ቀርጸው የሚያቀርቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን ሰይሟል።
በዚህም መሰረት፦
፩ኛ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ
፪ኛ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
፫ኛ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ
፬ኛ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
፭ኛ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል
፮ኛ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
፯ኛ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመሆን አጀንዳ የማርቀቅ ተግባራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚያቀርቡትን ረቂቅ አጀንዳ ከመረመረና ማስተካከያ ካደረገበት በኋላ የጸደቀውን አጀንዳ መሰረት በማድረግ በቅደም ተከተል እየተወያየ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።