ብፁዕ ዘይሌቡ ላዕለ ነዳይ ወምስኪን፤
እም ዕለት እኪት ያድኅኖ እግዚአብሔር ፤
ለችግረኛ እና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤
እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።
መዝ.፵ ፥ ፩

የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በእስር ላይ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ለአዲሱ ዓመት ፳፻፲፯ ዓ.ም መዋያ የሚሆን የበሬ ሥጦታ አበረከተ።
ምሥራቅ ሐረርጌ ,ኢትዮጵያ
ጳጉሜን ፭ ፳፻፲፯ ዓ/ም

የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረሪ ክልል ማረሚያ ቤት በሕግ ጥላ በእስር ላይ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ለ ፳፻፲፯ ዓ.ም ዓ.ም ለአዲሱ ዓመት የሰንጋ ሥጦታ አበረክቷል። በስጦታ ርክክቡ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፣መልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣መጋቤ አእላፍ ብንያም ጎንፋ የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊ ፣የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ተገኝተው የሥጦታውን ርክክቡን ተከናውኗል ።

በተያያዘም በብፁዕነታቸው እና በልዑካኑ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ለሆኑ የሕግ ታራሚዎች ጸሎታቸውን ምስጋናቸውን የሚያቀርቡበትን የጸሎት ቤት ጎብኝተዋል ለሕግ ታራሚዎችንም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትና ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል።© የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግኔኙነት ክፍል።