የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር ማድረግ እና ለሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት ይኖርብናል”። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ

September 10, 2024

“ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር ማድረግ እና ለሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት ይኖርብናል”።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ” የዘመናት ባለቤት እግዚአ ሰማያት ወምድር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ 2017 ዘመነ ማቴዎስ የምሕረት ዓመት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ” በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም:-
” አዲስ ዓመት፤ የዓመታት፣ የወራት፣የሳምንታት እና የቀናት ለውጥና መፈራረቅ ብቻ ሳይሆን ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር ማድረግ እና ለሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት እንዲሁም የለውጥን ሂደት ለመጀመር ቁርጠኛ መሆንን ይጨምራል።

ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ ቅን ልቡና፣ ቅን ሕሊና እሰጣችኃለሁ በማለት የሚነግረን፤ ዛሬ ላይ እንደ ደንጊያ ጽኑ እና ጨካኝ የሆነው ልባችን ቤተ ክርስቲያንን እና ምእመናንን እየጎዳ ይገኛል። ቅን ልቡና እና የተሰበረ መንፈስ ጠፍቶ በጎቻችንን በምድራዊ ሀሳብ እና በቁሳዊ ተራ እይታ መመልከት ከጀመርን ሰንብተናል።

በተለይም በአባቶች ደረጃ ለተጠራንበት ተልዕኮ መሥራት ካቆምን፣ ልጆቻችንን አስጨናቂ አገዛዝ ከጫንባቸው እና የምንመራቸው ልጆቻችን በምንከተለው ኃላ ቀር የመሪነት ዘይቤ ተሰላችተው ተስፋ ከቆረጡ ቆይተዋል። ለዚህ ድካማችን መፍትሔውም የድንጋዩን ልብ ከውስጣችን አውጥተን የሥጋን ልብ ለማግኘት መሥራት እንጂ ለዘመናት በኖረ መቋጠሪያ በሌለው ችግሮች ውስጥ ሆነን በኛ ድክመት የፈታነውን ሕዝብ ልዩ ልዩ እንቆቅልሽ እየፈጠርን ግራ ማጋባት ሊጠቅመው አይችልም።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን
ምእመናንና ምእመናት:-

አዲሱን ዓመት ስንቀበል በአሮጌው ዓመት የነበሩ የክፋት ሥራዎቻችን፣ የልዩነት መንገዶቻችን እና የጥፋት ዕቅዶቻችን በአዲሱ መንፈስ የሚሻሩበት፤ ከጨለማው አመለካከታችን ወጥተን የብርሃን መንገድን ልንከተል፤ ያለፈውን የጥፋት ሥራ ያበዛንበትን ዓመት በአዲሱ ዓመት በንስሐ ታጥበን ለእውነት ልንሰራ ይገባናል።

በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ። እንዲል መጽሐፍ ቅዱስ በክፋት ባረጀው ሰውነታችን አዲስ ዘመንን መጨመር ከኃጢአት ላይ ኃጢአትን መጨመር እና የኃጢአት ክምርን ማብዛት ስለሚሆን ምን ጊዜም አዲስ ዓመትን ስንቀበል በንስሐ እና በጎ ተግባርን በማብዛት ሊሆን ግድ ይለናል።

አዲሱን ዓመት ስንቀበል፤ ራሳችንን ለለውጥ በማዘጋጀት፣ ሰላምን በመስበክ፣ ክርስቲያናዊ ተግባራትን በማብዛት፣የተራቡትን በማብላት፣ የተጠሙትን በማጠጣት ሊሆን እንደሚገባ እያሳሰብን፤አዲሱ ዓመት የፍቅር፣የሰላም፣የአንድነት እና የስምምነት እንዲሆን እንመኛለን ፤በማለት አስተላልፈዋል።

+ አባ ሄኖክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ጳጉሜን ፭ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/abune-henok-cover.jpg 417 400 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-09-10 20:36:162024-09-10 20:36:16“ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር ማድረግ እና ለሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት ይኖርብናል”። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ኃላፊ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ! Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ኃላፊ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ! ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር... Link to: ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በእስር ላይ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ለአዲሱ ዓመት ፳፻፲፯ ዓ.ም መዋያ የሚሆን የበሬ ሥጦታ አበረከተ። Link to: ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በእስር ላይ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ለአዲሱ ዓመት ፳፻፲፯ ዓ.ም መዋያ የሚሆን የበሬ ሥጦታ አበረከተ። ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በእስር ላይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top