መስከረም 24 ቀን 2017ዓ.ም.
+ + +

በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለሚገኙ ሁሉምአብያተክርስቲያን ለሚመለከታቸው ኃላፊዎች ሥልጠና ተሰጠ።በሥልጠናውየሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ብርሃኑ ክፍሌ ዋና ፀሐፊው መልአከ ብርሃን ቀሲስ አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች የወረዳው ቤተክህነት ዋና ሥራአስኪያጅ ሊቀጠበብት መሠረት ይልማና ዋና ፀሐፊው ሊ/ኅእሸቱ የተሳተፉ ሲሆንከአንድ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪውን ጨምሮ ሦስት አባላትሥልጠናውን ተሳትፈዋል።

ሥልጠናውን ያዘጋጁት በሀገረ ስብከቱ የተቋቋመው የልማት ኮሚቴ አባላት ሲሆኑ ለሥልጠናው መሳካት ሁሉም አብያተክርስቲያናት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ሥልጠናውን በጸሎት የከፈቱት የሀገረ ስብከቱ ሥራአስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ብርሃኑ ክፍሌ ናቸው። በስልጠናው ባስተላለፉት መልዕክት በቀጣይ ለሚከናውን የልማት ሥራ መንገድ እንዲከፍት የሚያደርግና ቤተክርስቲያን በልማት ራሷን ችላ የገቢ አቅሟን እንድታሳድግ የሚያደረግ በመሆኑ የሚሰጠውን ሥልጠና ተከታትለው በአጥቢያቸው መተግበርና ውጤት ማምጣት እንዳለበቸው አሳስበዋል ።

ሥልጠናው በዶሮ እርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በሆልቲካልቸር ፣በወተት ላም እርባታ በከብት ማድለብ ፣በሰብል ልማትና በቢዝነስ ፕላን (በሥራ ላይ ዕቅድ) በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሥልጠናው ተሰጥቷል ።ተሳታፊዎችም ከሥልጠናው በቂ እውቀት እንዳገኙና በቀጣይ ለመተግበር እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።