የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የማጣራት ሥራው መሰረታዊ ዓላማ ግለሰቦችን ማሳደድ ሳይሆን ተቋምን መታደግ ነው።

October 4, 2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለው የመልካም አስተዳደር ችግር ከዚህ በላይ ሥር ሳይሰድና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሕልውና አደጋ በመሆን ጉዳት ከማድረሱ በፊት ችግሩን ከመሰረቱ በማጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር የሚያቀርብ ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ሥራ እንዲገባ አድርጓል።

ችግሩን ለማጥናት የሚደረገው ጥረትም ችግሩ የተፈጠረበት፣ ያደገበትና የጎለበተበት ቦታ ላይ መሆን እንዳለበት በሚገባ የሚያምነው ጠቅላይ ቤተክህነቱ አምስት መሰረታዊ ነጥቦችን በመለየት ማለትም፦

1. በሀገረ ስብከቱ የበጀት ዓመቱ ዓመታዊ እቅድና ሪፖርት ከገንዘብ ኃይል ቅጽ ጋር
2. የአስተዳዳሪዎች ዝውውር ዶክሜንት
3. የሰው ኃይል ቅጥር ፣ዝውውር፣እድገትና ስንብት
4. የፋይናንስ ሪፖርት የሀገረ ስብከትና የክፍለ ከተሞች
5. ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶችን ማግኘት የሚሉት ትኩረት ተደርጎባቸው እንዲጣሩ በአስተዳደር ጉባኤው በኩል ወስኗል።

ይሁን እንጂ ይህ የማጣራት ሥራው ትኩረት የሆነው
ባለ አምስት ነጥብ የትኩረት አቅጣጫ በቀጥታ የሚመለከታቸው የሀገረ ስብከቱ ባለሦልጣናት የጥናት አቅጣጫው ወደ አድባራትና ገዳማት የተነጣጠረና በአጥቢያ የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችን የግል የባንክ ሒሳባቸውን እስከ ማስመርመር የሚደርስ አደገኛ አካሔድ በጠቅላይ ቤተክህነቱ እየተሄደ በማስመሰል ደጋፊ ለማሰባሰብና አቅጣጫ ለማስቀየር በመጣር ላይ እንደሚገኙ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ይህን ፍፁም ሐሰትና መሰረተ ቢስ አሉባልታ በመንዛት የማጣራት ሂደቱን ለማወክ የሚጥሩ ወገኖች የሚሉትን የሚያምኑ አካላትም የማንም ሰው የሒሳብ ደብተር ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ ሊመረመር እንደማይችል ከመረዳት ጋር ጠቅላይ ቤተክህነቱ የግለሰቦችን የባንክ ሒሳብ የመመርመርና የማስመርመር ሥራ የመስራት ሃሳብ የሌለው መሆኑን እየገለጸ በዚህ አይነቱ አሰራር ዘላቂ የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግር ይፈታል የሚል የየዋሆች ስሌት ውስጥ የሚገባ እንዳልሆነ ለመግለጽ ይወዳል።

ስለሆነም አጣሪ ኮሚቴው ትኩረት ሰጥቶ የማጣራት ሥራውን የሚሰራው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተክህነት አሰራርና አሰራሩን ተከትሎ በተፈጠሩት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ብቻ መሆኑንም በአጽንኦት ይገልጻል።

ይሁን እንጂ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችን፣ ጸሐፊዎችን፣ሒሳብ ሹሞችን፣ቁጥጥሮችንና ገንዘብ ቤቶችን በተለየ መልኩ የባንክ ሒሳባቸው እንዲመረመር በማድረግ ለመወንጀል እየተንቀሳቀሰ ነው የሚባለው ጉዳይ ፍጹም መሰረተ ቢስና የማጣራት ሂደቱን በማጠልሸት ማጣራቱ ተቃውሞ እንዲገጥመው በማድረግ በውጤቱ ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ለመከላከል የተፈበረከ ወሬ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

በመጨረሻም ጠቅላይ ቤተክህነቱ ቤተክርስቲያን የቀደመ ክብሯን ለማስመለስ፣ከዘረኝነት፣ከሙስናና ከብልሹ አሰራር ጸድታ ለዓለሙ ተቋማት የተግባር ማሳያና ማስተማሪያ መሆን ትችል ዘንድ ብፁእ ወቅዱስ ፓትርያርካችን የሰጡንን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ በፍጹም ጽናትና ትጋት የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ብልሹ አሰራሩ ያስለቀሰና ያሳዘናቸውን ካህናት፣የካህናት ቤተሰቦች፣ ምዕመናንና ምዕመናትን የሚያስደስት፣እንባቸውን የሚያብስና ፍጹም የሚመኩበትን ተቋም ለመፍጠር እንደምንሰራና ለዚህም እግዚአብሔር አምላክ እንደሚረዳን እምነታችን የጸና ነው።

መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-10-04 07:19:062024-10-04 07:19:06የማጣራት ሥራው መሰረታዊ ዓላማ ግለሰቦችን ማሳደድ ሳይሆን ተቋምን መታደግ ነው።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ መመሪያ ሰጡ። Link to: ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ መመሪያ ሰጡ። ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ መመሪያ... Link to: በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት በልማት ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ!! Link to: በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት በልማት ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ!! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top