ሕዳር 19 ቀን 2017ዓ.ም
+ + +
በጉባኤው ብፁዕ አቡነ ሰላማ የሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሊቀ አእላፍ አባ ኃይለ ማርያም ያሳይ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም አበምኔት የወረዳ ቤተ ክህነት ሊቃነ ካህናት ሰራተኞች የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት የገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች የማኀበረ ቅዱሳንና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች የምእመናን ተወካዮች ተገኝተዋል። ጉባኤው ከህዳር 16 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ /ም የቆየ ሲሆን በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ እና የሁሉም ወረዳዎች ሪፖርት ቀርቦ ከተሰማና አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ
1 የካህናት ተልኮ እና መንፈሳዊ አገልግሎት በሀ/ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ
2 የመሪ እቅድ በሀ/ስብከቱ ዋናው ሥራ አስኪያጅ
3 የመረጃ አያያዝና እና አዘገጃጀት በሀ/ስብከቱ ዋና ጸኃፊ ስልጠና ተሰጥቷል ።
ሰልጣኞቹም በስድስት ክፍል ተከፍለው በሰፊው ተወያይተዋል ከተወያዩባቸውም ነጥቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ በአካባቢው በተከሰተው ግድያ እገታ የእርስ በእርስ መለያየት የንስሐ ቸባቶችና ልጆች ግንኙነትና ንስሐ አባቶች ልጆቻቸውን ጠንክረው እንዲጠበቁ እንዴት እናጠናክር የጠፉትንስ እንዴት እንፈልግ ::
ቤተ ክርስቲያን ከጥላ ዘቅዝቆ ልመና ለማላቀቅ ልማት እንዴት እናልማ እና ሌሎችም አንኳር አንኳር ነገሮች ተነስተዋል :: በመቀጠልም ከአንድ እስከ ሦስት የወጡ ተሸላሚዎች ኮምፒውተርና የተለያዩ የማበረታቻ ሽልማቶችን በመስጠት ከዚያም በመቀጠልም በዚሁ ዕለት በሀገረ ስብከቱ ርእሰ ከተማ መስመር ዳር በተገዛው 432 ካሬ ቦታ ላይ በ300 ካሬ ላይ ያረፈ ሁለገብ ባለ ሰባት ወለል ፎቅ ለመገንባት ታስቦ የመሰረት ድንጋይ በብፁዕ አቡነ ሰላማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ዻዸስ መሠረት ድንጋይ ተቀምጧል። በመጨረሻም ጉባኤው ባለ 18 የአቋም መግለጫ በማውጣት በብፁዕነታቸው ጸሎት ሰላምና መዳማመጥ በሰፈነበት መልኩ ተጠናቋል ::