የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የሚገኘውን ቤተ መጻሕፍት ወመዘክርን ገበኙ።
===================
ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም.
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለ ስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር ፕሮፌሰር አበባው አያሌው እና የሥራ ባልደረቦቻቸው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየምን ገበኙ።
ጉብኝቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅርሳቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ጋባዥነት የተዘጋጀ ሲሆን በጋራ ቅርሶቻችን ዙሪያ መሥራትን ዓላማው ያደረገ ነው ተብሏል።
ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ቤተክርስቲያን ካሏትን ቅርሶች ለመጠበቅ ካላት ጽኑ አቋም የተነሳ እያደረገች ያለችው ጥረት የሚመሰገን ቢሆንም ያሏትን ቅርሶች በዚህ ልዩ እንክብካቤ ማስቀመጧ ግን መልካም ነው ብለዋል።
ቅርስና ሕይወት አንድ ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ሁለቱንም ካጣናቸው ግን መልሰን አናገኛቸውም ። ስለዚህ መንከባከብ ያለብን ሳናጣቸው መሆኑን በመገንዘብ ቅድመ ጥንቅቃቄ ማድረግ አለብን በማለት አክለው ገልፀዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እስከዛሬ ቅርስ በመጠበቁ ረገድ አያሌ ሥራዎችን የሠሩ ቢሆን አሁን በዚህ ሰዓት ሕጋዊ የወረቀት ልውውጥ በማድረግ በጋራ ለመሥራት መሞከሩ ትልቅ እድል መሆኑን ገልፀው ወደፊትም በጋራ የሚያሠሩ የመግባቢያ ሰነዶች ን በመፈራረም የጋራ ቅርሶቻችን በጋራ እንጠብቃለን ብለዋል።
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ዋና ኃላፊ በኩረ ትጉሃን ምትኩ ከንቲባ በበኩላቸው ጥሪያቸውን አክብረው የተገኙትን የባለሥልጣኑ የሥራ ኀላፊንና የሥራ ባልደረቦቻቸውን አመስገነው በቅርስ ጥበቃ ዙሪያ በመተባበር እንደሚሠሩ ገልጸው ጉብኝቱ ፍጻሜውን አግኝቷል።