የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የ7ቱ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ8ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ማጠቃለያ በአሶሳ ሀገረ ስብከት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

August 5, 2025

ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም.

በመንፈስ ቅዱስ ጥሪ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አንብሮተ እድ ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ከተሾሙ ጳጳሳት መካከል ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል አንዱ ናቸው።

ብፁዕነታቸው በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩት ለነበረውና ለመጀመሪያ ጊዜ በስሙ ጳጳስ ለሚሾምለት ጋምቤላ ሀገረ ስብከት የተቀቡ እና ቅዱስ ሲኖዶስ በጠረፋማ ስፍራ የሚያሳዩትን መልካም አፈጻጸም ተመልክቶ ተጨማሪ ስድስት አህጉረ ስብከትን በመጨመር በኀላፊነት ሰጥቷቸዋል።

ብፁዕነታቸው በሁሉም አህጉረ ስብከታቸው ተወዳጅ፣ ተናፋቂና በስስት የሚመለከቷቸው እንዲሁም በሁሉም ማኅበረሰብ ዘንድ ከበሬታን ያተረፉ በመሆናቸው ከዕረቡ ሐምሌ 9 ቀን 2017ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2017ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በዝማሬ፣ በወንጌል አገልግሎት ፣በምግባረ ሰናይና በተለያዩ ሁኔታዎች ሲከበር ቆይቶ ዛሬ በአሶሳ ሀገረ ስብከት በእንዚ መካነ ገነት መድኀኔዓለም ወደብረ ማርቆስ ካቴድራል ክቡራን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የሥራ ኀላፊዎች የአሶሳ ሀገረ ስብከት የሥራ ኀላፊዎች፣ የአሶሳ ክልል መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተላቅ ድምቀት ተከብሮ ማጠቃለያውን አግኝቷል።

ይህ በዓለ ሢመት ከወትሮው ለየት የሚያደረግ ከሥጋዊ ድግስ ወደ መንፈሳዊ ድግስ ያደላ በመሆኑና ለብዙዎች ነፍስ መዳን ምክንያት ለመሆን የወንጌል አገልግሎትን ያዘጋጀ መሆኑ ነው።

ብፁዕነታቸው በበዓለ ሢመቱ ሲገልፁ ይህ ሢመት የእኔ ሳይሆን የቤተክርስቲያን ነው። በመሆኑም ሀሴት ማድረግ ያለባቸው የቤተክርስቲያን አካላት ናቸው። ለዚህም የደስታቸው ምንጭ እንዲሆን ወንጌል ይሰበክ፣ መዝሙር ይዘመር ያመኑ ሁሉ እየመጡ ሲጠመቁ በሰማይ መላእክት ዘንድ ታላቅ ደስታ ይሆናል ብለዋል።

ብፁዕነታቸው ከወንጌል አገልግሎት ባሻገር በክልሉ አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር በዓለ ሢመታቸውን አክብረዋል። ችግኞችን ስለ መትከልና መንከባከብ የሰውልጅ የመጀሪያ ሥራው መሆኑን በማውሳት ይህንን የጥንተ ተፈጥሯ ኀላፊነት ተግባራዊ ማድረግ አዲሱን ትውልድ ማስጠለል መቻል ነው ብለዋል።
የበዓለ ሢመቱን ማጠቃለያ በማዘጋጀት የአንበሳውን ድርሻ የወሰደው የአሶሳ ሀገረ ስብከት እድለኛ ሆነን ይህንን በማክበራችን ደስተኞች ነን በማለት ገልፀዋል።

በመጨረሻም ልዩ ልዩ በጎ ስጦታዎች ተበርክተው የበዓሉ ፍፃሜ ሆኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የሚገኘውን ቤተ መጻሕፍት ወመዘክርን ገበኙ። Link to: የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የሚገኘውን ቤተ መጻሕፍት ወመዘክርን ገበኙ። የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር... Link to: ዓመታዊ_የቁልቢ_ገብርኤል_ንግሥ በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ  ከገዳሙ አባቶች ጋር ዉይይት ተካሄደ። Link to: ዓመታዊ_የቁልቢ_ገብርኤል_ንግሥ በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ  ከገዳሙ አባቶች ጋር ዉይይት ተካሄደ። ዓመታዊ_የቁልቢ_ገብርኤል_ንግሥ በአል በሰላም ተከብሮ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top