ሰበካ ጉባኤ ማደራጃና ማስተባበሪያ መምሪያ

የመምሪያው ራዕይ 

በቃለ ዓዋዲ ደንብ በተደነገገው መሠረት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት እና አስተዳደር ተሸስሎ፣ ተጠናክሮና በተረካቢው ትውልው ዘንድ ተቀባይነት ኖሮት መመልከት ነው፡፡

ዓላማ

  • የቤተ ክርስቲያን የገቢ አቅም አድጎ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎች ተሠማርተው የሚያገለግሉ የካህናትና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ሕይወት እንዲሻሻልና የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ፍጹም እንዲሆን ማድረግ ፣
  • በእያንዳንዱ ሀገረ ስብከት ራስ አገዝ የልማት ሥራ ሊሠራ በሚቻልበት ሁኔታ እገዛ በማድረግ ጥሩ ውጤት እንዲመጣ መጣር ነው፡፡
  • ምእመናን በመንፈሳዊ እውቀት ጎልልምሰው በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው በክርስቲያናዊ ሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ፣
  • አህጉረ ስብከትና የተሻለ ገበ ያላቸው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በገቢ ራሳቸውን ችለው በገጠርግ በጠረፋማ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስትያናትን እንዲረዱ ማድረግ፣
  • ቤተ ክርስቲያን በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ያላትን አስተዋጽኦ ምእመናኑኑ ግንዛቤ የሚያገኙበትን ሥልጠና በመስጠት ሁሉም ክርስቲያኖች በእምነታቸው የፀኑና ጠንካራ ሆነው ማየት ናቸው፡፡

ተልዕኮ

  • መምሪያው የተቋቋመበትን ተቋማዊ አሠንግ በማጠናከር ሕገ ቤተ ክርስቲያንና ቃለ ዓዋዲው ጨምሮ ቤተ ክርስቲያናችን እንድትመራባቸው ቀድሞ የወጡ ደንቦች እየተሠራባቸው የሚገኙት መመሪያዎች ወደፊትም የሚመጡ ሕጐችና ደንቦች በእያንዳንዱ ሀገረ ስብከት ወረዳና በአጥቢያ ደረጃ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ተገቢው የሰበካ ጉባኤ ሥራ እንዲሠራ ተግቶ መንቀሳቀስ፣
  • በእያንዳንዱ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ ገዳማት አድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በቃለ ዓዋዲው መመሪያ መሠረት ተደራጅተው የቤተ ክርስቲያናችንን ሀብትና ንብት ቅርስ ጠብቆ ሁሉም አገልግሎት በጭ በጋራ እንዲተዳደር ማድረግ፣
  • ችግሮች እንዳይከሰቱ ማስተማር ከተከሰቱም በደንቡና በመመሪያው መሠረት ሊፈቱ የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

እሴት

  • ካህናትና ምዕመናንን በቅን ማገልገል፣
  • የቤተ ክርስቲያናችንን ዶግማና ቀኖና ጠብቆ ማስጠበቅ፣
  • የቤተ  ክርስቲያናችን ሀብቶች እንዲጠበቁ በግልፀኝነት መሥራት፣
  • የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሥራቸውን በግልፀኝነትና በተጠያቂነት እንዲሠሩ ማመቻቸት፣
  • በሰበካ ጉባኤ አባልነት የሚመረጡትን በሥነ ምግባር የታነፁ እንዲሆኑ ሥልጠና መስጠት ናቸው፡፡