ገዳማት አስተዳደር መምሪያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ፣ ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ብሔራዊት እንደመሆኗ የሀገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ሲወሳ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉልህ አስተዋጽኦ በቀዳሚነት ይነሳል፡፡

ከዚህም ጋር ቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በምድረ በዳና በተራራ በአትን አጽንተው በመጋደል ያቆዩልን የቅድስና አሻራ ሳይጠፋ ገዳማቱ የጾም፣ የጸሎት ፣ የበረከት ፣ የቅርስና የታሪክ ደሴቶች ሆነው ለሚቀጥለው ትውልድ በክብር እንዲተላለፉ ከታሪክነታቸው ባሻገር የቱሪስት መስህብና የምርምር ማእከላት ጭምር እንዲሆኑ ለማስቻል እና በገዳማቱ የሚገኙ መነኮሳትም ራሳቸውን ችለው ፣ በተደራጀና በተረጋጋ መልኩ ዓሰረ ምናኔያቸውን ፣ መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ከግንቦት 18 ቀን 1992 ዓ/ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የገዳማት አስተዳደር ምሪያ ተብሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተቋቁሟል፡፡

ሰለሆነም መምሪያው የተቋቋመበትን ዓላማ ተግባራዊ ላማድረግ እቅድ አቅዶ ፣ በጊዜ ሰሌዳ ለይቶ መሥራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከመምሪያው ተልዕኮና ግብ አንጻር በበጀት ዓመቱ ሊከናወኑ ለታቀዱት ዝርዝር የሥራ ተግባራት ማስፈጸሚያ የበጀት ፍላጎትን በማካተት ከተጨማሪ የሰው ኃይል አደረጃጀት ጋር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1.2 የመምሪያው ርእይ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስር ያሉ ገዳማት በክብ ተጠብቀው ትውልድ ተሸጋሪ ሆነው እንዲቀጥሉ ማስቻልና በትውልዱ ውስጥ የገዳማትን ክብርና መንፈሳዊ ታሪካዊ ጠቀሜታቸውን ማስረጽ

1.3 የመምሪያው ተልዕኮ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት ታሪካዊ፣ ሐዋርየዊት ብሔራዊትና ዓም አቀፋዊት የሆነች እንደመሆኗ መጠን ስራ ያሉ ጥንታዊ ገዳማት ከሚያበረክቱት መሠረታዊና መንፈሳዊ አገልገሎት በተጨማሪ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የልማት እንቅስቃሴያቸውና ጠቀሜታቸው እንዲጎላ ማድረግ በየጊዜው የሚከሰተውን ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ክስተት በቅርበት እየተከታተሉ ችግሮቻቸውን መቅረፍ በገዳማት ያሉትን መናንያን መንከባከብና መከታተል

1.4 የመምሪያው ግብ

ገዳማት የቅድስና ምንጭነታቸው ተጠብቆ እንዲቀጥል ከዚያም በሚፈሰው በረከት ትውልዱ እንዲቀደስና እንዲባረክ ማድረግ

1.5 የመምሪያው እሴቶች

  • ለዓቂበ ሃይማኖት ፣ለገዳማዊ ሕይወት
  • ራስን መስጠት
  • ፍቅረ እግዚአብሔር ፍቅረ ቢጽ
  • እምነት
  • ተስፋ
  • ጽናት
  • ትሕትና
  • ጥበብ
  • ፍትሕ
  • ቅንነት
  • ተጠያቂነት
  • ግልጸኝነት
  • ልማት
  • ሰላም