ግንቦት 27ቀን 2017 ዓ/ ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሦስት ዓመታት የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ዋና ፀሐፊ ሆነው የተመረጡ መሆኑን ይታወቃል ይህንን ምክንያት በማድረግ ለሁለቱም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የእንኳን ደስ ያላችሁ መርሐ ግብር የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም አበው መነኮሳት ፣ዲያቆናት እንዲሁም ልዩ ልዩ ሰራተኞች ደስታቸውን ገልጸዋል ።
በመርሐ ግብሩ ላይም ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አብነ አብርሐም የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስያትል እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል ።
ቀደም ሲል ሁለቱም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በዚሁ ታላቅ ገዳም በተለያየ ኃላፊነት ያገለገሉ እና የገዳሙ ባለውለታ እንቁ አባቶቻችን ከመሆናቸውም በላይ ይህንን ትልቅ ኃላፊነት መቀበላችሁ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ወደተሻለ ደረጃ ያደርሷታል በማለት የገዳሙ አበው መነኮሳት ደስታቸውን ገልጸዋል ።
በመጨረሻም ሁለቱም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለተደረገላቸው ልዩ መርሐ ግብር ምስጋና በማቅረብ በጸሎት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል ።
©ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም