የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ሊቃውንቱ ፣ገዳማውያኑ እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የጠያቀችሁትን የእርቅና ሰላም ሐሳብ ተፈጻሚ እንዲሆን የሚቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። (ቅዱስነታቸው በመዝጊያው ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ)

June 8, 2025

በዘርፈ ብዙ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲያደርግ የቆየው 14ኛው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ በቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ እና ባለ 12 አንቀጽ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል ።
+ + +
ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም.
ከሉላዊነት (Globalization) ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቀ ወጣቱን ዓርነት ለማውጣት አየሠራ የሚገኘው ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምርህት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ለ14ኛ ጊዜ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ አያደረገ ነው። 14ኛው ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ከመላ ሀገሪቱ የተሰበሰቡ የሰንበት ትምርህት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኀላፊዎች ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ተቀዳሚ ምክትሎችና ምክትሎች የሚሳተፉበት ሲሆን ትናንት ግንቦት 30 ቀን 2017ዓ.ም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ዓመታዊ ሪፖርት በማድመጥ ተጀምሯል ። በመቀጠልም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን አባታዊ መልእክት አድምጧል ። ጉባኤው የአህጉረ ስብከት ጠቅለል ያለ ዓመታዊ ሪፖርት ካደመጠ በኋላ ከላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት አድርጓል።

ከውይይቱ በመቀጠል የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ሦስተኛውን ስልታዊ እቅድ ትግበራ ላይ የውይይት መነሻ ሐሳብ ቀርቦ ጉባኤው ተወያይቶበታል። ጉባኤው ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2017ዓ.ም. የቀጠለ ሲሆን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሱታፌ ለቤተክርስቲያን፣ የአንድነቱ የትኩረት አቅጣጫዎች ማለትም በየወረዳው የአደንድነት ጉባኤዎችን ማጠናከር ፣ያልታተሙ መጻሕፍቶችን ለኅትመት ማብቃት ፣ስርዓተ ትምህርቱን ሁሉም ቦታ ተደራሽ ማድረግ ፣ስልጠናዎችን ማዘጋጀት የውስጥ መመሪያዎችን መደንገግ ሚዲያና ቴክኖሎጂ በማበልፀግ ማናበብ መቻል እና በአቋም መግለጫ የቀረበውን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ መሆኑ ተገልፆ በሀገረ ስብከት ተወካዮች የቀጣይ ዓመት ትግበራዎች ላይ ውይይት አድርጓል። ከውይይቱ በተጨማሪም ብፁዓን አባቶች ትምሀርተ ወንጌል ሰጥተዋል።

ከዚህም ባሻገር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮ መሠረት ታትሞ ለኅትም የበቃው ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍ በዘንድሮው ዓመት በአፋን ኦሮሞ እና ከ5ኛ እስከ 7ኛ ክፍል የሚያገለግል የመማሪያ መጽሐፍም በአማርኛ ታትሞ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተብራርቶ ለምርቃቱ ግን ልዩ ዝግጅት ለማዘጋጀት እንደታሰበ ተገልጿል።
በመጨረሻም ጉባኤው በአቋም መግለጫው በልዩ ልዩ ሥፍራ የተፈጠሩ ልዩነቶች በእረቀ ሰላም እንዲፈቱ እና የመሪ እቅድ ትግበራው ተፈጻሚ እንዲሆን በአጽንዖት ጠይቋል።

የጉባኤን በሰላም መጠናቀቅ ተከትሎ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሰጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በዓለ ጰራቅሊጦስ ቤተክርስቲያን የተሠራችበት እና ሐዋርያት ኃላፊነት የተቀበሉበት ልዩ ቀን መሆኑን ገልጸው በዚህ ቀን ወጣቶች ከቤተክርስቲያን ኃላፊነት ለመውሰድ በየዓመቱ መሰብሰባቸው መልካም ነው ብለዋል። በቤተክርስቲያን አላስፈላጊ ነፋስ እንዳይገባ ተግቶ የሚጠብቀው የሰንበት ትምርህት ቤት ወጣቶች መሆናቸውንም አክለው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በአቋም መግለጫው ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ሰላምን ማስፈን የዘወትር ጸሎቴ ነው። ነገር ግን ብቻየን የማደርገው አይደለም። በሁሉም በኩል ለሰላም የሚከፈለውን ዋጋ መክፈል ይጠይቃል። ነገር ግን በእኔ በኩል የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ያሉ ሲሆን እንደ ዓይን ብሌን የምንመለከተውን መሪ እቅድም ተፈጻሚነት እንዲኖረው የበኩሌን ጥረት አደርጋለሁ ብለዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የመልካም ምኞት መግለጫ መርሐ ግብር በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተከናወነ Link to: ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የመልካም ምኞት መግለጫ መርሐ ግብር በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተከናወነ ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና... Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጸሕፈት ቤት መምሪያና ድርጅቶችን ጎበኑ። Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጸሕፈት ቤት መምሪያና ድርጅቶችን ጎበኑ። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመንበረ ፓትርያርክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top