አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
***
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዕ አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የድል በዓል ተከበረ ።
በዓለ ንግሡ የምስካየኅዙናን መድኃኔዓለም ታቦት ከስደት የተመለሰበትን ወቅት ምክንያት በማድረግ ዛሬ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ,ም በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሯ።
ታቦቱ ህጉ በቅዱስነታቸው መሪነት ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሥርዓተ ዑደት ከተደረገ በኋላ በገዳሙ የሰንበት ት/ቤት እና በተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ወረብ ቀርቧል ፣ በዕለቱ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ የኬንያና የምስካየኅዙንን መድኃኔ ዓለም ሊቀ ጳጳስ የበዓሉን ታሪካዊ ጉዞና መንፈሳዊ ይዘት መሰረት በማድረግ አባታዊ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በብፁዕ አቡነ ቶማስ ነአዊ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ዕለቱን በተመለከተ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማናት ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ሕዝበ ክርስቲያኑ በሃይማኖቱ እንዲጸና፣በዓላቶችን ከማክበር ጎን ለጎን ስጋ ወደሙን ፣መቀበል የመንግስቱ ወራሽ ለመሆን እንዲተጋ አደራ ካሉ በኋላ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአገር ሰላምና ደህንንነት ተግቶ በመጸለይ ፈጣሪውን እንዲለምን አደራ በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተው የበዓሉ ፍፃሜ ሆነዋል ።
በበዓለ ንግሱ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣የቅዱስነታቸው ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ፣ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የመሪ ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎችና ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት በታላቅ ዴምቀት ተከብሮ ውሎአል።