መስከረም 16 ቀን 2016ዓ.ም.

በበዓሉ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅና የየክፍል ኀላፊዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና መላው የከተማው ምዕመናን ተገኝተዋል።

የከተማው ከንቲባ በዓሉን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ። በመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሪነት የደመራ መለኮስ ስነ-ስርዓት ተካሂዶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል ብለዋል ።

መረጃው የመተከል ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።