የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሮ ዋለ።
************
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
********
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++

የቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሢመት ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣አምባሳደሮች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል ።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት”ሁላችንም ውሉደ ክህነት በውል ልንገነዘበው የሚገባ ዓቢይ ቁም ነገር፣ ኣሁን ባለን ቁመና ቤተ ክርስቲያንን በሚፈለገው ደረጃ ወደ ቀጣዩ ትውልድ በአስተማማኝ ሁኔታ ማሸጋገር ያዳግታል፤ካሉ በኋላ ላለንበት ዘመን የማይመጥኑ ብዙ የስራ ኣፈጻጸሞች አሉብን፤ እነዚህን ከምር ኣውቀን በማስተካከል ወደ ተሻለ የስራ አፈጻጸም ካልተሻገርን በምድርም፣ በሰማይም፣ በታሪክም፣ በኅሊናም ተወቃሽ ከመሆን ኣናመልጥም፤በማለት ዘመኑን የሚመጥን ሥራ መስራት እንደሚገባ አበክረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በበዓለ ሢመቱ አከባበር ወቅት ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦

ከሁሉ በፊት ለመላው ውሉደ ክህነትና ሕዝበ ክርስቲያን እግዚአብሔር እንኳን ለዐሥራ ሁለተኛው ዓመት በዓለ ሢመተ ክህነት አደረሳችሁ እንላለን፤

“አአኵተከ አባ አግዚአ ሰማያት ወምድር አስመ ኃባስኮ በዝንቱ አምጠቢባን ወስማትምራ ወከሠትኮ ሰሕፃናት አወ አባ አስመ ከማሁ ኮነ ሥምረትከ በቅድሜከ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ኣባት ሆይ! ይህጓጓ ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ሰሕዓናት ስሰ ገስጥህሳቸው ኣመሰግንሃለሁ፤ ኣዎን አባት ሆይ! ፈቃድህ በፊትህ አንዲህ ሆኖኣልና”(ማቴ.፲፩÷፳፭-፳፮)

የጌታችን ዐኔመኝነትይህ የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስክርስቶስ ትምህርተ ወንጌል ነው፤ ጌታችን በዚህ ኣስተ ምህሮው የሰማዩና የምድሩ ጌታና አባት ፈቃድ ምን እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦልናል፤

ይኸውም የእግዚአብሔር ፈቃድ፣ የመንግሥተ እግዚአብሔርን ምሥጢር ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስን የማወቅ ዕድል፣ እናውቃለን እንራቀቃለን ከሚሉ ጥበበኞችና አስተዋዮች መሰወር፤ በአንጻሩ ደግሞ እንደ ሕፃናት የዋሃንና ንጹሓን ለሆኑ ምእመናን መግለጽ እንደሆነ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ የማይናወጥ ፈቃድ ነው፤ትልቁ የእግዚአብሔር ጥበብና ምስጢር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ኣበክሮ ይነግረናል፤እግዚብሔር አምላካችን ዓለም ይህንን ምስጢርና ጥበብ ኣውቆ አምኖና ተቀብሎ መጻኢ ዕድሉን እንዲያሳምር ይጐተጕታል፤ ጌታችን በአካለ ሥጋ በዚህ ዓለም ተገልጾ በሚያስተምርበት ጊዜ ይህ ጥበብና ምስጢር የተሰወረባቸው የማኅበረ ሰብ ክፍሎች ነበሩ፤ ምስጢሩ ሊሰወርባቸው የቻለው በጥበባቸውና በዕውቀታቸው የመመካት ችግር ስለነበራቸው እንደሆነ ቃሉ ይጠቁማል መቼም እኛ ሰዎች በሥልጣን፣ ወይም በዕውቀት ወይም ደግሞ በሀብት በአጠገባችን ካሉ ሰዎች የተሻልን፤ነን ብለን ስናስብ የትዕቢት መንፈስ ይወረናል፤ ትዕቢት ደግሞ እውነትንና ዓቅማችንን እንዳናውቅ ኣእምሮኣችንንበመሽበብ ለሰዎች ሓሳብና ሰብእና አክብሮት እንዳንሰጥእንደሚያደርገን የታወቀ ነው፤

በወቅቱ ጠቢባንና አስተዋዮች ነን የሚሉ የአይሁድ አለቆችና መሪዎችም በዚህ ደካማ ሰብኣዊ ጠባያቸው በራሳቸው ዕውቀት ስለተማመኑ የእግዚብሔር ጥበብናጎን ምሥጢር የሆነውን ክርስቶስን ለማወቅና ለመቀበል ዝንባሌውና ፍላጎት ኣልነበ ራቸውም፤ፍላጎት ኣልነበራቸውም፤ በመሆኑም ፍላጎት ላለው ጨምሮ መስጠት ለሌለው ግን ያለውንም መንሣት ጠባዩ የሆነ እግዚአብሔር አምላክየነበራቸውንም ጨርሶሰውሮባቸዋል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ምስጢሩን ከትዕቢተኞች መሰወር ለትሑታን ግን መግለጽ በመሆኑ ነው፤

በጌታችን ኣስተምህሮ እዚህ ላይ ሕፃናት እየተባሉ ያሉ የእሱን መሲሕነት አውቀው ኣምነውና ተቀብለው ከእርሱ ጋር ይጓዙ የነበሩ አይሁዳውያን ተከታዮቹን ነው፤ እነሱ በቅንነትና በትሕትና እንዲሁም የዕውቀት ሕፃናት እንደሆኑ አውቀው የበለጠ ዕውቀትን ከሱ ለማግኘት ፍላጎት ስለነበራቸው እሱነቱን ገለጸላቸው፤
ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ጥንትም ሆነ ዛሬ የነበረ ያለና የማይለወጥ ቀዋሚ ፈቃዱ ነው፤ ከዚህ አንጻር ዛሬም ቢሆን ጥበቡን ከትዕቢተኞች ይሰውራል ለሕፃናት አማንያን ግን ይገልጻል፤

ዛሬም እንደቀድሞው ዓለም በዕውቀቷ በሥልጣንዋና በሀብቷ እየተመካች ለእግዚአብሔር ቃል ጆሮ ዳባ ልበስ ስላለች ምስጢሩና ጥበቡ ተሰውሮባታል፤ከክርስቶስ ጥበብነትና ምስጢርነት ይልቅ ምርጫዋ የጨለማው ገዥ ጠባያትን መቀበልና ማስፋፋት ምርጫዋ ሆኖአል፤

ለዚህም ተግባርዋ የተመሳሳይ ፆታ ነውረ ኃጢኣትና የአምልኮ ባዕድ እምነቶች ሕጋዊ ዕውቅና እንዲያገኙ የምታደርጋቸው ጥረቶችንና ለኔ ለኔ በሚል የስግብግብ አመለካከት የምታካ
ሂዳቸው ኣውዳሚ ጦርነቶች ዋና ዋና ማሳያዎች ሆነው ይገኛሉ፣ የሰው ልጅም ከነዚህ እኩያት ተግባራት በነፍሱ ብቻ ሳይሆን በሥጋዊ ኑሮውም ቢሆን ከጉዳት በቀር ቅንጣት ታህል ጥቅም ማግኘት እንደማይችል ማወቅ ተስኖታል፣ እግዚአብሔር ግን የዚህ ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንደሆነ አጠንክሮ ነግሮናል፣ ታድያ የዓለም ጥበብና ዕውቀት በእግዚአብሔር ፊት ይህን ያህል ሞኝነት ከሆነ እኛ ሕፃናት ኣማንያን ምን እየሰራን ነው? የሚለው ተስእሎት የዚህ ዕለት ኣንኳር ጥያቄአችን ሊሆን ይገባል፤

ከሁሉ በፊት እግዚብሔር ይህንን የክርስቶስን ምስጢርነት የገለጸልን ሕፃናት ሆነን በመገኘታችን እንደሆነ ከእርሱ የበለጠ መስካሪ ኣያስፈልገንምና እሱን ኣጥብቀን እንጨብጥ፣ ቀጥሎም በዚህ ቅዱስ ፈቃዱ ሕፃናት የሆነው እኛን በልዩ ምርጫው ፓትርያርክ፣ ሊቀ ጳጳስ ፣ኤጲስ ቆጶስ፣ ቀሲስ፣ዲያቆን፣ ምእመንና ማእምንት በሚል ሰይሞ በመንግሥቱ ውስጥ እንድናገለግል የተቀበለን መሆኑን ለአፍታ እንኳ አንዘንጋ፤በጎቹን በንጽህና እና በቅድስና እንድንጠብቅ፣ በምድር ላይ ሰላምና ሰላም ብቻ እንድናውጅ፣ ፍትሕ ርትዕ እንዳይዛባ እንድንመክር፣ ኣንድነትና እኩልነት እንዳንነጣጥል፣ ፍቅርና ይቅርታ እንዳይቀዘቅዝ ሌት ተቀን እንድናስተምር የሰላም ወንጌልን አስጨብጦናል፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ በቤቱ ቤተኛ ሆነን እንድናዝና እንድናዝዝ ኣድርጎናል፤ ታድያ በቤቱ ሆነን የምንሰጠው አገልግሎት ለባለቤቱ የሚመጥን እንዲሆን ያስፈልጋል፤ ተገልጋዮች ምእመናንም በአገልግሎታችን ደስተኞች መሆናቸውን ማረጋገጥ ኣለብን፤

ሁላችንም ውሉደ ክህነት በውል ልንገነዘበው የሚገባ ዓቢይ ቁም ነገር፣ ኣሁን ባለን ቁመና ቤተ ክርስቲያንን በሚፈለገው ደረጃ ወደ ቀጣዩ ትውልድ በአስተማማኝ ሁኔታ ማሸጋገር ያዳግታል፤ ላለንበት ዘመን የማይመጥኑ ብዙ የስራ ኣፈጻጸሞች አሉብን፤ እነዚህን ከምር ኣውቀን በማስተካከል ወደ ተሻለ የስራ አፈጻጸም ካልተሻገርን በምድርም፣ በሰማይም፣ በታሪክም፣ በኅሊናም ተወቃሽ ከመሆን ኣናመልጥም፤

ከላይ ጀምሮ እስከታች ያለው ውሉደ ክህነት ከዚያም መላው ሕዝበ ክርስቲያን በዚህ ላይ የበኩሉን ኃላፊነት ለመወጣት በርትቶ እንዲሰራ ያስፈልጋል፤

ሌላው እኛ የሃይማኖት አገልጋዮች ሃይማኖትን ስንጠብቅ ሕዝብን ይዘን ነው፤ ያለ ሕዝብ ሃይማኖት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፤ የሕዝብም መኖር ያለሰላም አይታሰብም፤ ሃይማኖት እንዲኖር ሕዝብ መኖር አለበት፤ሕዝብ እንዲኖር ሰላም መኖር አለበት፣ እነዚህ የማይነጣጠሉ ናቸው፤ አሁን ባለንበት ጊዜ ግን ፈተናቸው
በዝቶአል፤ ስለሆነም በሕዝቦች አንድነትና ሰላም በፍትሕና እኩልነት ላይ አጥብቀን እንድናስተምር የወቅቱ ኣባታዊ ጥሪያችንና መልእክታችን ነው፤

እግዚአብሔር መልካም በዓለ ሢመተ ክህነት ያድርግልን!

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ”
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርአሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲ወ፯ ዓ.ም.
ኣደስ አበባ አቶዮጵያ