የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ትምህርተ ሃይማኖትን የያዘ መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በአሜሪካ ታትሞ ተመረቀ፤ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ አንባብያን በቅርቡ በኢትዮጵያ እንደሚታተም ተገለጸ።

February 27, 2025

የመጽሐፉ አዘጋጅ ነዋሪነታቸውን በሰሜን አሜሪካ ያደረጉት ቀሲስ ዶክተር አምሳሉ ተፈራ ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት ለምረቃ የበቃው አዲሱ መጽሐፋቸው “The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Over the Centuries: History, Worship and Doctrine” የሚል ርዕስ የያዘ ሲሆን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ እና መሠረተ እምነት በዝርዝር የሚዳስስ በዓይነቱም በይዘቱም ለየት ያለ መጽሐፍ እንደሆነ ታውቋል።

ስለ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የሚናገሩ መጻሕፍት በግእዝ በስፋት የሚገኙ በአማርኛ ቋንቋ የተተረጎሙ እና በሌሎችም የሀገሪቱ ቋንቋዎች እየተጻፉ የሚገኙ ሲሆን በእንግሊዝኛ የተጻፉ ግን በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ናቸው። ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ይህንን ክፍተት ለመሙላት አስበው የተነሡ ሲሆን የመጽሐፉም ጠቀሜታ ስለኢትዮጵያ ቤ/ክ ሥርዓተ አምልኮና ዶግማ ዘመኑን በዋጀ መልኩ በእንግሊዝኛ በውጭው ዓለም ለሚገኙ በተለይ ለወጣቶች ማስተማሪያ በእጅጉ ወሳኝ መጽሐፍ መሆኑን መምህራን ተናግረዋል።

ይህ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የቤተክርስቲያን ታሪክና ነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የተመረቀ ሲሆን የመረቁትም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፤ የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ናቸው። ሁለት ምሁራን በመጽሐፉ ላይ የዳሰሳ ጥናት ያደረጉ ሲሆን፤ የመጽሐፉ አዘጋጅ ለሁሉም ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

በዕለቱም የዋሽንግተን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤት ዘማርያን፣ ምዕመናን እና ምዕመናት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።በአሁኑ ሰዓት መጽሐፉ በአማዞን (Amazon) ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡
  • አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ከተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!
  • “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
  • የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስገነባው 1B+G+8 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።
  • የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መ/ዮንቨርሲቲ ተካሔደ።

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ Link to: መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ በዓለ ሢመት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሮ ዋለ። Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ በዓለ ሢመት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሮ ዋለ። በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top