የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አዲሱን የጀርመን አምባሳደር በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

March 20, 2025

መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የሆኑት ዶክተር ፈርድናንድ ቮን ዌይሂ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የተመደቡበትን የሥራ ኃላፊነት ለመጀመር ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡

አምባሳደሩ እንደተናገሩት “ለእኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበለጠ መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም በዚህች ሀገር ውስጥ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማወቅ ለብዙ ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለዚህ እኔም በተያዘልኝ ቀጠሮ መሠረት ከጀርመን ኤምባሲ በመምጣት ከቅዱስ ፓትርያርኩም ቡራኬ ተቀብዬ ስለ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለማወቅ ችያለሁ” ብለዋል፡፡

አምባሳደሩ አያይዘውም “በአሁኑ ወቅት የዐቢይ ጾም ወቅት በመሆኑ፤ ኦርቶዶክሳውያን በጾም፣ በጸሎት በየአብያተ ክርስቲያንቱ ነው ያሉት፡፡ ይህ ሥነ ሥርዐት በጀርመን ሀገር ከምናየው የተለየና አስደናቂ ነው፡፡ በተዘዋወርኩባቸው ቦታዎች ሁሉ በተለይም አብያተ ክርስቲያናት በሚገኙባቸው ቦታዎች በየዕለቱ ሰው በቤተክርስቲያን ይገኛል፣ የሚሰማው የቅዳሴ ድምፅ የተለየ ነው፡፡ይህ በጣም አስደናቂ ተሞክሮ ነው።” ብለዋል፡፡

አምባሳደሩ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር በትብብር ስለሚሠሩት ሥራም አብራርተዋል “የልምድ ልውውጥ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ መጥቀስ የምፈልገው ነገር ቢኖር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ጋር ስለ ደን ጥበቃ በትብብር የምንሠራው ሥራ አለ፡፡ በኢትዮጵያ ክልል በአየር ስትበሩ አንዳንድ አረንጓዴ ጥቅጥቅ ያሉ የደን ደሴቶችን ታያለህ። በዚህ ደሴት መካከል ቤተክርስቲያን አለች፡፡ ቤተክርስቲያን ደኖችን ጠብቃ ያቆየቻቸው ናቸው፡፡ ሰዎችም ቤተክርስቲያኗ የምታስተምረውንም ስለሚሰሙ ዛፎችን አይቆርጡም፡፡ ስለዚህ ስለ ደን ጥበቃ የቤተክርስቲያኗ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡እኔ እንደማስበው እነዚህን አረንጓዴ ደሴቶች በመሬት ገጽታ ላይ ማስቀመጥ እና የበለጠ ማማስፋት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እናም ይህንን አረንጓዴነት በመደገፍ አብረን እንሠራለን” ብለዋል፡፡

በመጨረሻም አምባሳደር ዶክተር ፈርድናድ ቅዱስነታቸው በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ስላነጋገሯቸው፣ በተደረገላቸው አቀባበልና ቅዱስነታቸው ስለሰጧቸው ቡራኬ አመሰግነዋል።

©EOTC T.V.

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ በዓለ ሢመት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሮ ዋለ። Link to: በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ በዓለ ሢመት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ተከብሮ ዋለ። በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ... Link to: ወደ ግሪክ አቴንስ የተጓዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑካን ቡድን ለበርካታ ዓመታት የቆየውን አለመግባባት በሰላምና በእርቅ መቋጨቱን ገለጸ። Link to: ወደ ግሪክ አቴንስ የተጓዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑካን ቡድን ለበርካታ ዓመታት የቆየውን አለመግባባት በሰላምና በእርቅ መቋጨቱን ገለጸ። ወደ ግሪክ አቴንስ የተጓዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑካን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top