መስከረም ፳፩ ፳፻፲፯ ዓ/ም
+ + +
“አንቲ ውእቱ ታቦት ዘትጸውሪ ትእዛዘ
ሙሴ የዋህ ዘኢየአምር ጋእዘ
ዕፀ ኢንቁዘ ዘአግበረ ለኪ ድንባዘ
ወእብነ ወርቅ ርብዐ ለድንባዝኪ ምእኃዘ”
ክርክርን የማያውቅ ቅን ሰው ሙሴ ከማይነቅዝ ዕንጨት መሎጊያንና ለመሎጊያሽ መያዣ የሚኾን አራት የወርቅ ደንጊያን ያሠራልሽ ሕግን ትእዛዝን የምትሸከሚ ታቦት አንቺ ነሽ።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
በምሥራቅ ሐረርጌ ሀ/ስብከት የብዙኅን ማርያም በዓለ ንግሥ በደከር ደ/ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀ/ስብከት ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም መ/አእላፍ ቀሲስ ብንያም ጎንፋ የሀ/ስብከቱ ዋና ጸሐፊ የሀ/ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች የገዳማት እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።