ጳጉሜን 3/2016 ዓ/ም
================
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከትና የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ጸሐፊ መግቤ ሥርዓት ዳንኤል ጌታቸው፣የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ኃላፊዎች፣የሀዋሳ ከተማና ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ላዕከ ወንጌል ቀሲስ ደግፌ ባንቡራ፣የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ምእመናንና ምእመናት የተገኙ ሲሆን ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ ክፍል አንድ በጋቤ ምሥጢር ቆሞስ አባ  ሠርጸ ሚካኤል የባሌ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ፣ ክፍል ሁሉት በዲያቆን ብርሃን አድማስ ትምህረተ ወንጌል ተሰጥቷል።

ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ መሪነት እጅግ በፍጥነትና በጥራት እየተገነባ ወዳለው ጠበል ቤት በመሄድ ጸሎት ከተደረገ በኋላ በብፁዕነታቸው ተባርኮ ወደ ዐውደ ምህረት በመመለስ ሥርዓተ ዑደቱ እንደ ተጠናቀቀ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን በቅደም ተከተል ያሬዳዊ ወረብ ቀርቧል።

በመጨረሻም ብፁዕ  አባታችን አቡነ ዮሴፍ  የዛሬው በዓል በሁለቱም መምህራን የተገለጠ በመሆኑ በሰማነው ቃል ፍሬ ማፍራት ከቻልን በቂ ነው።    ምክንያቱም እኛ ላልፈጠርነው ሰውነት ከመጨነቅ ይልቅ ምድራዊውን ረስተን ሰማያዊ አስበን መኖር አለብን።

የዛሬው በዓል አንድም ነገረ ምጽአቱ የሚታሰብበት ሲሆን ምጽአት ደግሞ የሠራነውን የምንቀበልበት ካልሠራንም የምንቀጣበት ስለሆን ሰማያዊውን አስቡ የሚል አባታዊ መልእክት አስተላልፈው በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል ሲል የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ለመንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት  ሕዝብ ግነኙነት መምሪያ  በላከው መረጃ አሳውቋል።