ግንቦት ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””
ባህርዳር -ኢትዮጵያ
የባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ገዳም ያስገነባው ባለ ስድስት ወለል ሁለ ገብ ሕንፃ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ግግቦት ፳ ቀን ፳ ፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ተመርቋል።
በዚሁ ጊዜ ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት:-” ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ ገቢዋ ከሙዳየ ምጽዋት ሳይሆን እንደዚህ ያለ ልማት በማልማት መሆን አለበት ብለዋል። “ይህ ሕንፃ ጊዮርጊስ እንግዶችን ለመቀበያ የሚያገለግል ሲሆን አገልግሎቱ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በጠበቀ መልኩ የሚያከናውን ይሆናል ብለዋል።
በምረቃውም የባህር ዳር ሀገረ ስብከትና የወረዳው ቤተ ክነት ሠራተኞች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ምዕመናንና ምዕመናት ተሳታፊዎች ነበሩ።ሲል የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባደረሰን ዘገባ ገልጿል።