በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ የተሞከረውን መፈንቅለ ሲኖዶስ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ።
**********
የካቲት ፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
**********
በኖርዌይ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ካህናትና ምእመናን በቅርቡ የተሞከረውን የመፈንቅለ ሲኖዶስ ሙከራ የሚያወግዝና የኢትዮጵያ መንግሥት ሲኖዶሱን ለመክፈል መከራ ላደረጉ አካላት እየሰጠ ያለውን እውቅና የሚቃወም ሰላማዊ ስልፍ አደረጉ። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ብሎም ከሀገረ ስብከታቸው በተሰጠው መንፈሳዊ መመሪያ መሠረት ወደ አደባባይ የወጡት በመላዋ ኖርዌይ የሚኖሩ ካህናትና ምእመናን በኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ደጃፍ እና በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቀኖናዋን ለማስከበር የሄደችበትን ርቀት እና መንግሥት ሰአርያነ ቀኖና የሆኑ አካላትን በመደገፍ ቤተክርስቲያናችንን አየጎዳ እንደሆነ ለኖርዌይ መንግሥት እና ለዓለም ሕዝብ አሳይተዋል።