ታሕሳስ 13 ቀን 2017ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሽገር ከተማ ሀገረ ስብከት በቡራዩ ገፈርሳ ጉጄ መልካ ኖኖ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኙት የአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች እና የማህበራት አመራሮች የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር እንዴት መከበር እንዳለበት ከወዲው ሊከናወኑ በሚገቡ ጉዳዮች ዙርያ በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል።
በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ወቅትን ጠብቀው ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ የጥምቀት በዓል ነው፡፡ እንደ ሊቃውትን ትርጉሜ ጥምቀት ማለት መነከር መዘቅ ፣መታጠብ ፣ መረጨት ማለት ነው፡፡በዓሉን የተለየ የሚያደርገው በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ወንዝ ወርደው ለማረፊያ በተዘጋጀላቸው ቦታ ያድራሉ፡፡ ህዝበ ክርስቲያኑ በነቂስ ወጥቶ ታቦታቱን በማጀብ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በመሄድ ያከብራሉ፡፡ ካህናት ሌሊቱን በማህሌት ስብሐተ እግዚአብሄር ሲያደርሱ ቆይተው የቅዳሴው ስነ ሥርዓት በመንፈቀ ሌሊት ተጀምሮ ይፈጸማል፡፡ ይሁን እንጂ ለበርካታ ዓመታት ይህንኑን ታሪካዊ በዓል ለማክበር ወደ አዲስ አበባ ገዳመ ኢየሱስ ሲወጡ የነበሩት ታቦታት በእግዚአብሔር አጋዥነት በድንግል ማርያም አማላጅነት በብፁዕ አባታችን አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ያላለሰለሰ ጥረት አዲስ የጥምቀት ማክበርያ ቦታ አግኝተን በመንግስት በኩል ከፍተኛ እገዛ እየተደረገልን በፍጹም ደስታ እያከበርን እንገኛለን። ከዚህው ጋር ተያይዞ ይህንን የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር ከአምናው በተሻለ መልኩ ተዉቦ እና ደምቆ እንዲከበር ከወዲው ዝግጅት ስለ ሚያስፈልግ በዛሬው እለት ከአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም
1ኛ ከወይበላ ማኅደረ መለኮት ቅድስት ማርያምእና ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል
2ኛ ከፊሊ ዶሮ አቡነ ተክለ ሃይማኖትቤተክርስቲያን
3ኛ ከደብረ በረከት ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን
4ኛ ከአሸዋ ሜዳ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን
5ኛ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ቤተ ክርስቲያን የተወጣተጡ
የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች የስብከተ ወንጌል አገልጋዮች፣ የሰንበት ትምህርት ተወካዮች እና የማህበራት አመራሮች በቦታው ተገኝተው ቦታውን ከማጽዳት ጀምሮ እንዴት መከናወን እንዳለበት መክሮዋል።
የዚህ ውይይት ዋና አላማው የጥምቀት በዓል ሲመጣ የተለለያዩ ሀገራት ቱሪስቶች ፣ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች እና ባለስልጣናት በዓሉን ከእኛ ጋር ለማክበር ወደ ተቀደሰችው አገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሚመጡ እዉን ነው ስለዚህ በዩኒስኮ ከተመዘገቡት የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥምቀት አንዱ ቢሆንም በባለቤትነት ደረጃ ግን የምትመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስለ ሆነች ከወዲው መዘጋጀት እና የሚመጡትን እንግዶች ፍጹም በሆነ ክርስቲያናዊ መልክ ልንቀበላቸው ስለሚገባ ይህንንም ለማሳሰብ ጭምር ነው ተብሎአል። በዚህ እና መሰል ጉዳዮች ዙርያም ከቤቱ ሐሳብ አስተያየት የሰጡት ታላላቅ የገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የማህበር ተወካዮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሲሆኑ በሰጡት አስተያየታቸውም ለሀገራችን ኢትዮጵያዉያን አንድነትና ተቻችሎ የመኖር ተምሳሌት ጥምቀት አንዱ ማሳያነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ወጣትም ከወዲው ለሰላም እና አንድነት ዘብ ሊቆም ይገባል፡፡ ከወዲው ከልጆቻችንን ጋር ሁነን የከተራና ጥምቀት በዓል በየአመቱ ሲመጣ ታቦታት ወደ ማረፊያቸው የሚሄዱበትንና የሚያርፉበትን ጎዳናዎች ለማጽዳት እና ለማስተካከል በተባበረ ክንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንሰራለን ብለዋል። አክለውም ምዕመናኑ ፤ባህላቸውን፣ ሃይማኖታቸውን ሥርዓታቸውን እና ትውፊታቸውን ጠብቀው ከቀደምት አባቶቻቸው የተረከቡትን በረከት ለልጆቻቸውም ማስረከብ አለባቸው ብለዋል። የዛሬው የጥምቀት በዓል አከባበርን በተመለከት በታቦቱ ማክበርያ ቦታ የተደረገው ውይይት በፀሎት ተጀምሮ በስኬት ተጠናቋል ።