ሐምሌ ፲፭፣ ፳፻፲፯ ዓ/ም
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከበረዉን የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግሥ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ በሚከበርበት ቁልቢ ከተማና ከአጎራባች የፀጥታ አካላትና የገዳሙ አስተ የሥራ ኀላፊዎች ጋር ዉይይት ተካሂዷል።

በዓሉን ለማክበር ወደ ቦታዉ ለሚመጡ ምዕመናን ሰላምና ደህንነታቸዉ ተጠብቆ እንዲያልፍ በቋሚና በተመላላሽ ጥበቃ እንዲሁም የትራፊክ ፍሰቱ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሱን ኀላፊነት መወጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የፀጥታ ሥራዉን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ከፌደራል ፖሊስ ፣ከኦሮሚያ ፖሊስ፣ከድሬደዋ ፖሊስ እንዲሁም ከሐረሪ ፖሊስ ጋር በጋራ በመቀናጀት እንደሚሠራም ተገልጿል።

በተያያዘም ቀደም ሲል ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀ/ስብከት ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለኢ.ኦ.ተ.ቤ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት በስልክ በዓሉ ያለምንም ጸጥታ ችግር በዓሉ እንዲከበር ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በቂ ቅድመ ዝግጅት መካሄዱን መግለጻቸው የሚታወስ ነው።