የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአራት ኪሎ እና ፒያሳ የምታስገነባቸው አዳዲስ ሁለገብ ሕንጻዎች የንድፍ ሥራ ርክክብ ተካሄደ።

August 5, 2025

ሐምሌ ፲፮ ቀን፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
*****

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአራት ኪሎ እና ፒያሳ የምታስገነባቸው አዳዲስ ሁለገብ ሕንጻዎች የንድፍ ሥራቸው ተጠናቅቆ ርክክብ ተካሄደ፡፡

አራት ኪሎ ላይ የሚገነባው በ6,000 ካሬ ላይ የሚያርፍ ባለ 12 ወለል ሕንጻ ሲሆን፤ እስከ 4ኛው ወለል ለንግድ አገልግሎት፣ ቀሪው ደግሞ ለመኖሪያነት ያገለግላል፡፡ በተመሳሳይ በፒያሳ የሚገነባው በ1,686 ካሬ ላይ የሚያርፍ ባለ 7 ወለል ሕንጻ እስከ 3ኛው ወለል ለንግድ አገልግሎት፣ ቀሪው ደግሞ ለመኖሪያነት እንዲያገለግል ታስቧል፡፡

የሕንጻዎቹን ንድፍ ኢ ኢ ኤስ ኮንሰልቲንግ አርክቴክት እና ኢንጂነሪንግ ፒ ኤል ሲ በተባለ ድርጅት ተካሂዶ፤ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተረክበዋል፡፡

በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ የሕንጻዎቹ የንድፍ ሥራ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለሥራው የደከሙትን ሁሉ አመስግነዋል፡፡ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ከዚህ በኋላ ወደ ሥራ ለመግባት ምንም የቀረ ነገር የለም ፤ ወደፊት ነው እንጂ ወደ ኃላ የለም” ሲሉ የሕንጻ ግንባታውን ለመጀመር በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በኩል ያለውን ቁርጠኝነትና ዝግጁነት አስታውቀዋል፡፡

በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፣ የማይጨው አላማጣና ራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የጠቅላይ ቤተክህነት ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የንድፍ ሥራው ለግንባታው ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ጠቅሰው፡- ‹‹ሥራው በመጠናቀቁ እድለኞች ነን፡፡ አባቶቻችን በሥጋ ሳይሆን በነፍስ ተጠቃሚ ሁነው፤ ያቆዩልንን ሐብት፤ ቤቶች፤ መሬት፤ እኛም ቤተክርስቲያኗን የተረከብን የዚህ ዘመን ትወልድ አልምተን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር እንሠራለን›› ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

የሕንጻዎቹ ዲዛይን ከዘመናዊነት ባለፈ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትውፊት የተላበሱ እንዲሆኑ ተደርጎ መዘጋጀቱ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡ በአራት ኪሎ እና ፒያሳ የሚገነቡት ሁለቱ ሁለገብ ሕንጻዎች “ሕንጻ አበው” እና “ዝክረ ቅዱሳን” ተብለው የተሰየሙ ሲሆን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ዓመታዊ_የቁልቢ_ገብርኤል_ንግሥ በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ  ከገዳሙ አባቶች ጋር ዉይይት ተካሄደ። Link to: ዓመታዊ_የቁልቢ_ገብርኤል_ንግሥ በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ  ከገዳሙ አባቶች ጋር ዉይይት ተካሄደ። ዓመታዊ_የቁልቢ_ገብርኤል_ንግሥ በአል በሰላም ተከብሮ... Link to: የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በቡግና ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖት ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ Link to: የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በቡግና ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖት ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በቡግና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top