በሰው ፊት ለሚመሰክርኝ ሁሉ እኔም በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ። ማቴ 10:-32
የከሚሴ ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤል ሰበካ ጉባኤ ሁለት ደብርን በአንድ ሰበካ ጉባኤ ስር የሚያስተዳድር ሲሆን በዓመት ውስጥ 7 ዓመታዊ በዓላትን ያከብራል።ዛሬም በወርኀ ሐምሌ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤልና የህፃኑ የቅዱስ ቂርቆስና የእናቱን የቅድስት ኢየሉጣ ዓመታዊ ቀዓል የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞችና የወረዳው ቤተ ክህነት ሰራተኞች እንዲሁም የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት እና ህዝበ ክርስቲያኑ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በእለቱም በወረዳው ቤተ ክህነት ስ/ወንጌል ክፍል በሰው ፊት ለሚመሰክርኝ ሁሉ እኔም በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እመሰክ
ርለታለሁ በማለት በማቴ10:-32 ያለውን የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በማንሳት የሰማእትነትን እና በሰማእትነት የሚገኘውን ዋጋ በሰፊው በእለቱ የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን በበዓሉ ለመጡ ምእመናን ቃለ ወንጌልን አስተምረዋልበመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በመልአከ ገነት የጀን ተስፋዬ ቃለ ምእዳን ተደርጎ የበዓሉ ፍጻሜ ሁኗል።© የከሚሴ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል