መስከረም 17/2017 ዓ.ም ባሕር ዳር
በዓሉም ብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃም ጋባዥነት በብፁዕ አባታችን አቡነ ሰላማ የምዕራብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመራ ሲሆን ልክ እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ በደመቀ መልኩ በዓሉ በሰላም ተከብሯል።
ብፁዕነታቸው ስለሰላም አስፈላጊነት ትኩረት እንድንሰጠውና የመስቀሉን ሰላም ሁል ጊዜ ልናስብ ይገባል ብለዋል ። እሌኒ ንግስት መስቀሉን እንደፈለገችው እኛም የጠፋውን ሰላም እንፈልገው በማለት ህዝበ ክርስቲያኑን ራሱን እኔ የሰላም ተምሳሌት ወይስ የጥፋት ብሎ እንዲጠይቅ አድርገውታል።
በመጨረሻም ይህ ዘመን ሰላም የሚሆንበት ዓመት እንዲሆንልን ሁላችን እንጸልይ ብለው የደመራ ቡራኬ ተባርኮ ደመራው ተለኩሷል።
መረጃው የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።