ሐምሌ ፯ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””
ሰሜን አሜሪካን -ኦማሀ
****
በሰሜን አሜሪካን የኮሎራዶና አካባቢው ሀገረ ስብከት አምስተኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ሐምሌ ፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም በኦምሐ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን መካሔድ ጀመረ።

ጉባኤውን በቃለ በረከትና በጸሎተ ምዕዳን የጀመሩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኮሎራዶና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጻጻስ በህብረት፣በስምምነትና በአንድነት በመቆም ለቤተክርስቲያን ሰበበካ ጉባኤ መጠናከርና መስፋፋት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።አያይዘውም በውጪው ዓለም የምንገኝ ሁላችንም ለአገራችን ለቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ተግተን ልንጸልይ ይገባል ሲሉ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መልአከ ብርሀን ዘለዓለም መንግስቱ ኮሎራዶና አካባቢው ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው
የቤተክርስቲያንን አንድነት ለማጠናከርና ተቋማዊ ሥራዎችን በማከናወን እድገት ማስመዝገብ ይቻል ዘንድ እንዲህ አይነት ጉባኤዎችን ማካሔድ አስፈላጊ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል ብለዋል።

ጉባኤው በዛሬው እለት በጸሎት የተጀመረ መሆኑንና የገለጹት የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሔኖክተገኝ ጉባኤው በነገው ዕለት ሪፖርቶችን ካዳመጠ በኋላ በሪፖርቶቹ ዙሪያ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ከገለጹ በኋላ በጉባኤው ላይ ለተሳተፉ አካላትም የምስክር ወረቀት ይሰጣል በማለት የጉባኤውን በይፋ መጀመር አብስረዋል።