ፍርድ ቤቱ የሕገወጥ ቡድኑን መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከጠየቀችው ዘጠና ቀናት ውስጥ የ፵፭ ቀናት የእግድ ትዕዛዝ ወሰነ።
የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመው ሕገወጥና ኢቀኖናዊ ድርጊት ምክንያት በሕግ አግባብ የሚፈቱ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ መብት እና የአማኞችን ሁለንተናዊ መብት እንደከበር ያስችል ዘንድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች የጠበቆች ኮሚቴ በማቋቋም ጉዳዮችን በሕግ አግባብ እንዲፈቱ እየጠየቀችና እየተከታተለች እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ መሠረት የጠበቆች ቡድኑ ዛሬ የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ/ም በዋለ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ችሎት የሰጠውን የተለያዩ ውሳኔዎችን በጥልቅ ማብራሪ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም ፍርድቤቱ የቤተ ክርስቲያኗን ሕጋዊ ጥያቄ በሕግ አግባብ መልካም ውሳኔ የሰጠበት መሆኑን ግልጽና ጥልቅ በሆነው ገለጻው ተጠቁሟል።
የጠበቆች ቡድኑ በመግጫው ሕገወጦቹ ያቀረቦቻው የመቃወሚያ ጉዳዮች እንደነበሩ አብራርቶ ፍርድቤቱ በውሳኔ ውድ አድርጓቸዋል ብሏል።
ፍርድቤቱ ውድቅ ካደረጋቸው መቃወሚያ መከራከሪያ ነጥቦች መካከል
፩. ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ሰውነት ያላት በመሆኑ የመክሰስና የመከሰስ መብት የለት መሆኑንና በጉዳዩ ላይ ክስ መመስረት እንደምትችል።
፪. ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን የመብት ጥሰት የንብረት ባለቤትነት ያለው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ማየት የሚችል መሆኑ በመጥቀስ የሕገወጡ ቡን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድ አድርጓል።
በአጠቃላይ በሕገወጡ ቡድን የቀረቡ መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረግ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጡ ሹመት ላይ በተሳተፉ ፳፮ቱ ግለሰቦች ላይ ክስ እንድትመሠርት ውሳኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ በጠየቀችው የሦስት ወር እግድ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤቱ ፵፭ ቀናት ከሦስቱ “አባቶች” በስተቀር ፳፮ (26)ቱም ግለሰቦች
ከዚህ ቀደም የገቡበትን መንበረ ጵጵስና እና አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ “የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሏትን ይዞታዎች፣ አህጉረ ስብከት፣ገዳማት እና አድባራት፤ አብያተ ክርስቲያናት ንብረቶቿን፤ ታሪካዊ ቅርሶች፣ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ መገልገያ እንዳይጠቀሙ፣ ወደ ቅጥሯ እንዳይገቡ፤ ንብረቶቿን እንዳይወስዱ፣ እንዳይገለገሉ፣ ዓርማዋንና ስሟን እንዳይጠቀሙ ይህ ጊዜያዊ የዕግድ ትዕዛዝ ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀናት ብቻ (ከየካቲት ፫/፳፻፲፭ ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ድረስ ብቻ ተሰጥቷል”።
መባሉን የጠበቆች ቡድን በመግጫው አሳውቋል።
ከዚሁ ጋር የኦርዶክሳውያን የእስር ሁኔታ የተነሳ ሲሆን በአብዛኛው እየተፈቱ መሆናቸውን ጠቅሶ በሻሸመኔና በአርሲ ነገሌ አካባቢ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን እስረኞ ለመጋቢት ፯፳፻፲፭ ዓ/ም ፍርድ ቤት እንደተቀጠሩም ተጠቅሷል።
በዚህ ረገድ የሕግ ተርጓሚ አካላት ላይ የሚታየው ፍትሕን የማስፈን ተጠቃሽ ሥራዎችን በመመዘርዘር በፍርድ ቤቶች የሚስተዋለው ፍትሕን የማስፈን መንገድ የሚበረታታና የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሰው የጠበቆች ቡድኑ በአስፈጻሚ አካላት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የታየው የፍረድ ቤቶችን ውሳኔ ያለማስፈጸም ሁኔታዎች በእጅጉ ሊታረሙ እንደሚገባም ገልጿል።
በሌላ በኩል “በፓስተር ዮናታን” እና “በፓስተር ኢዩ ጩፋ” የቀረበው ክስ ምን ላይ ደረስ? ለሚለውም በምላሹ ከዚሁ ጋር ጎን ለጎን እያስኬደው እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የጠበቆች ቡድኑ የሕጉን መንገድ ተከትሎ የቤተ ክርስቲያን መብትና ማስጠበቅ ሁነኛ ግቡ መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን ይሁን እንጂ የትኛውም መንገድ ይሁን ድርጊት ከቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ከአባቶች ቃል የማይቀድምና የማይበጥል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የምትከተላቸውን የይቅርታና የስምምነት አቅጣጫዎችን በማክበረ እንደሚቀጥል ገልጿል።