**********
ታህሣሥ ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግሥ በአዲስ አበባ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ሚያዝያ ፳፫ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ,ም በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከበረ ።

በዚሁ ጊዜ ታቦተ ህጉ ከመንበሩ በመውጣት ሥርዓተ ዑደት ከተደረገ በኋላ በደብሩ ሊቃውንትና ወጣት የሰንበት ት/ቤት አባላት ወረብ ቀርቧል ፣  በዕለቱ በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳስ በዓሉን በማስመልከት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ለበዓሉ ታዳሚዎች ከሰጡ በኋላ  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማናት በዓሉን የሚመለከት አባታዊ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ የበዓሉ ፍፃሜ ሆነዋል ።ዜናውንና ፎቶግራፍ ያደረሱን መ/ሰ አባ ኪሮስ ወልደአብ ናቸው።