ልማት በቤተ ክርስቲያን
ልዮ ዕትም መጽሔት
ይህ ”ልማት በቤተክርስቲያን“ የተሰኘ ልዮ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጌታችን፣ የአምላካችን፣ የመድኀኒታችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንዲውል ላደረጋችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጋናዋን ታቀርባለች፤
በአጠቃላይ የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓላችን ፍጹም መንፈሳዊና ደማቅ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንዲውል ልዩ ልዩ ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላትና የተለያዩ ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን ያደረጋችሁትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ቤተክርስቲያናችን በልዩ አድናቆት የምትመለከተው ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ምስጋናዋን ታቀርባለች።
በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ላይ ብቻ ያተኮረ ምላሽ እንዲሰጥ መመሪያ ተላለፈ።
በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ የሚተላለፉ መልእክቶች የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ላይ ብቻ ያተኮሩ እንዲሆኑ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ አስተላልፈዋል።
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ከሚከበሩ የአደባባይ በዓላት መካከል የጥምቀት በዓል አንዱና ዋነኛው ነው። በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የአደባባይ መንፈሳዊ በዓላችን የጥምቀት በዓል ዘንድሮም በታላቅ ሥነሥርዓት የሚከበር ሲሆን በዓሉ በደመቀና ባማረ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነት ዐቢይ ኮሚቴ ተጀራጅቶ በየዘርፉ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በሀገረ ስብከታቸው የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናክረው ቀጥለዋል።
* በዋጃ አካባቢ ደብረ ሣሌም ቦታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ለሚታነጸው ሕንፃ ቤተክርስቲያን የአንድ መቶ ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
* አዲስ የተሰራውን የአየር ማረፊያ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ቅዳሴ ቤት አክብረዋል፤ሃያ ሺህ ብር የበረከት ልገሳ አድርገዋል።
*በኮረም ከተማ ለሚታነጸው የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኑረዋል።የአንድ መቶ ሺህ ብር ድጋፍም አድርገዋል።
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጋምቤላ ገቡ፤ከአሥር ሚሊየን ብር በላይ ንዋያተ ቅዱሳን ይዘው ተጉዘዋል።
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላ ፣ የቄለም ወለጋ፣ የአሶሳ እና የደቡብ ሱዳን አሁጉረ ስቅከት ሊቀ ጳጳስ የጋምቤላ ክልልና የቤንሻንጉል ጉምዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት የኃማኖት ተቋማት ሰብሳቢና የልማትና የሰላም አምባሳደር ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ተነስተው በመኪና ጉዞ በማድረግ ከ10,000,000 ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ልዩ ልዩ ንዋተ ቅድሳትን በመያዝ ወለጋ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን እየባረኩና የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን በማስከፈትና የንዋተ ቅድሳት ድጋፍ በመድረግ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጋምቤላ ገብተዋል ።
ቅዱስ ፓትርያርኩ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ለሚያስገነባው ባለ ሰባት ወለል ሕንጻ የመሠረት ደንጊያ አስቀመጡ።
በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሚመራው ፣የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የካህናት ማሰልጠኛ ሆኖ ከዘመናዊ ትምህርት ቤት እስከመንፈሳዊ ኮሌጅና ኃላም ከፍተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነገረ መለኮት ወይም ቲዎሎጂ ትምህርት ማስተማሪያ ፣የጥናትና ምርምር ማዕከል ሆኖ ለ60 ዓመታት ያህል መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠቱ ይታወቃል።
የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል በ22 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የእንጀራ ማምረቻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ።
የእንጀራ ማምረቻው በሒደት ከስድስት ሺህ እስከ አስር ሺህ እንጀራ የሚያመርት መሆኑ ተገልጽዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡብ እና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ፣ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክርና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ አላማጣ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
ከሦስት ዓመታት በፊት የቋሚ ሲኖዶስ ተረኛ መሆናቸውን ተከትሎ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት የመጡት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በአዲስ አበባ ለመቆየት በመገደዳቸው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሳይሔዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል ጥንታዊ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ ሁኔታ ሰላማዊና ደማቅ በሆነ መልኩ እንዲከበር ሁሉም ወገን በኃላፊነት መንፈስ እንዲሠራ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አሳሰቡ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓልን በማስመልከት “ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ ሰላምን እሻ ተከተላትም” (መዝሙር ፴፬፥፲፫) የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኀይለ ቃል መነሻ በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት የጥምቀት በዓል ጥንታዊና ሃይማኖታዊ መሰረቱን በጠበቀ መልኩ ሰላማዊ በሆነና በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ በኃላፊነት መንፈስ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባው ገልጸዋል።
የብፁእ አቡነ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ ጉዞ በቤተ ክርስቲያን ሕግ እና ሥርዓት መሠረት የተፈቀደ ነው።
ብፁእ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኔዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገረ ስብከታቸው የጥምቀትን በዓል ለማክበር መጓዛቸው ይታወቃል። ጉዟቸውን በተመለከተ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተናፈሰ ያለው ወሬ እጅግ የተሳሳተ ሲሆን የብፁእነታቸው ሐዋርያዊ ጉዞ በቤተ ክርስቲያን ሕግ እና ሥርዓት መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነ እና በቅዱስ ፓትርያርኩ የተፈቀደ መሆኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስታውቋል።