ቅርስ ጥበቃና ቤተመጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ጽ/ቤት የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በዘመናዊ መልክ ተደራጅቶ የማስጎብኝቱን ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በውስጡም የንዋየ ቅድሳት እና የተለያዩ ታሪካዊ እና ኃይማኖታዊ መጻሕፍትና ድርሳናትን በአንድ ላይ በማሰናዳት ለጎብኝዎች ፤ለጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውሉ ተደረትገው ለጉብኝት ዝግጁ በመሆን አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል ፡፡ የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ሶስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህም፡.-የቅርስ ጥበቃ -ቤተ-መጻሕፍት -ቤተ-መዘክር የሚሉት ናቸው፡፡
በቤተ መዘክሩ የታችኛው ወለል የተለያዩ መጻሕፍቶች፣ ሃይማኖታዊ ታሪካዊ ሰነዶች ፤ የሚገኙ ሲሆኑ፡- በላይኛው የቤተመዘክሩ ወለል ደግሞ የቅዱሳን ፓትርያርኮች የመገልገያ ንዋየ ቅድሳት (የእጅ መሰቀል፤ የመጾር መሰቀል …ወዘተ.) ፎቶግራፎች በአግባቡ ተደራጅተው ለጎብኝዎች ዝግጁ ሆነው የተሰናዱ ናቸው፡፡ በ2014 ዓ/ም በጀት ዓመት በመምሪያው በእቅድ ተይዘው የተከናወኑትን እና ሳይከናወኑ የቀሩባቸውን ምክንያቶች (ችግሮች) አስመልክቶ ዝርዝር የሥራ ሪፖርት እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
፩.- በ2014 ዓም የተሠሩ ሥራዎች
- ከባሕልና ቱሪዝም፣ ከቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን እንዲሁም አዲስ አበባ ቱሪዝም ቢሮ እና መሰል ተቋማት ጋር በመቀናጀት ቅርስን አስመልክቶ ለመምሪያው ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡
- በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አዲስ የታተመው የግዕዝ መጽሐፍ ቅዱስ በቁጥር 20 የሚሆኑ ለቤተመጻሕፍት አገልግሎት በነጻ ለሙዚየሙና ለቤተመጻሕፍት አገልግሎት እንዲውል ደብዳቤ ተጽፏል፡፡
- 25የሚደርሱ የወሎ ዮኒቨርስቲ የግዕዝ ዲፓርትመንት ተማሪዎች የብራና መጻሕፍትን በማየትና ወደፊት ለምርምርና ጥናት አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ በርካታ ጥንታዊ የብራና መጻህፍቶች እንዳሉ እና አጠቃላይ ቤተመጻሕፍቱን በመጎብኝት ለቀሩት ማኅበረሰብ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ታሪክና ቅርስን የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚሰሩና ቃል ገብተዋል፡፡
- በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ላልይበላ አስተዳደሪ ቆሞስ አባ ጽጌ እና ከቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ፤ የዩኒስኮን አፍሪካ ዋና ጸሐፊ እና ተወክለው በመጡ የውጭ ሃገር ሰዎች ጋር በመገኛኝት የቅዱስ ላልይበላን ቅርስ ከጦርነቱ በኃላ ያለበትን ሁኔታና ወደፊት ስለሚጠገኑት አብያተ ክርስቲያናት የፕሮጀክት ሥራ ውይይት ተደርጓል፡፡
- ሙዚየሙን የማስጎብኝትና ቤተመጻሕፍቱን (Library) ለተጠቃሚዎች ክፍት በማድረግ የተለመደውን የዘወትር አገልግሎቱን ለሁሉም ማኅበረሰብና በተገቢው መልኩ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
- ከመንግስት መ/ቤት ማለትም ከቤተመጻሕፍት ወመዘክር ጋር ወደፊት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ (Memorandum of Understanding) ተዘጋጅቶ ወደሥራ ለመግባት ዝግጁ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
- የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እና ብፁዐን አበው አባቶች (ሊቃነ ጳጳሳት) አረፍተ ዘመን ሲገታቸው መጻሕፍቶቻቸው የመባረኪያ የእጅ መስቀላቸውና የመሳሰሉት ወደ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር በሕጋዊ ደብዳቤ ገቢ እንዲሆን ተደረጓል ፡፡