መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻ ወ ፲፯ ዓ.ም
በዓሉ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ክቡር መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ እማምሰው (ቆሞስ) የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ጸሐፊያን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ካህናትና ዲያቆናት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተክብሯል።
በበዓሉም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ ገበየው ጥላሁን ሌሎች የካቢኔ አባላትና የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ተገኝተዋል።
ከየአጥቢያው የተወጣጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤተ ወጣቶች የዕለቱን በዓል በተመለከተ ያሬዳዊ ወረብ አቅርበዋል
በመጨረሻም በብፁዕነታቸው ቃለምዕዳንና ቡራኬ ተሰጥቶ ደመራው ተለኩሶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል
መረጃው የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።