ጥር 20 ቀን 2017.ዓ.ም.
=================
ሜትሮ ፖሊታን ማር ዩልዮስና ፋዘር ጆሲ ጃኮብ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ ሣልሳዊ መልዕክትን በመያዝ የመጡ ሲሆን የልዑካኑ መምጣት ዋነኛ ዓላማ  ከዚህ በፊች ከአኀት አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመንፈሳዊ አገልግሎት፣ በጤና ዘርፍ ፣ በትምህርት ዘርፍ እና በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ የነበረውን የጋርዮሽ  ስምምነት በኮሮና ምክንያት የተቋረጠ ቢሆንም ዳግም በነበረው ስምምነት ላይ መቀጠል የሚያስችል ውይይት ለመድረግ  እንደሆነ ተገልጿል። በተለይም  በውጭው ዓለማት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  እና የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ  ቤተክርስቲያን  የጋራ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ያለመ ነው ተብሏል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በልዑካኑ መምጣትና በገንቢ ሐሳቡ መደሰታቸው በመግለጽ በስምምነቱ መሠረት መተግበር እንደሚቻል የገለፁ ሲሆን ልዑካኑን በመላክ ስምምነቱ እንደገና እንዲጀመር ስላደረኩ የሕንድ ማላንካሳ ኦሮቶዶክስ ፓትርያርክን  አመስግነዋል።
በቅዱስነታቸው ምላሽና አቀባበል የተደሰቱት ልዑካኑ
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ ሣልሳዊ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የተላከ ስጦታ ያበረከቱ  ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ  ከዚህ ልዑክ ምላሽ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።
በውይይቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  እና የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሚገኙባቸው የውጭ ሀገራት አንዱ ባንዱ የመገልገል እንድል የሚያመቻቹበት ሁኔታም እንደሚኖር  ተገልጿል።  ልዑካኑ አክለው እንደገለፁት በዐረብ ሀገራት ላይ ቤተክርስቲያንን ለማስፋፋት ያደረገችውን ጥረት በማድነቅ በሌሎች ክፍላተ ዓለማት ለምታደርገው እንቅስቀሴ ለመደገፍ ከጎን መሆናቸውን በማረጋገጥ ቃለቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የማተጠቃለያ ሐሳብና ለልዑካኑ የበረከት ስጦታ በመስጠት ውይይቱ ተጠኗቋል።