የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የ”ዝክረ ኒቅያ ዓለም አቀፍ ጉባኤ” ከሚያዚያ 20-24 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ ሊቃውንት ጉባኤ አስታወቀ።

February 1, 2025

ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም
****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“”””””””””””””””””””””

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ጉባኤ ጥር 23ቀን 2017 ዓ.ም “የዝክረ ኒቅያ ጉባኤን” ዓለም አቀፍ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ለማካሔድ መርሐ ግብር መያዙ ይታወሳል።

ሆኖም ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ማካሔድ ይቻል ዘንድ መርሐ ግብሩን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ በማስፈለጉ ጉባኤው ከሚያዚያ 20-24 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲካሔድ መወሰኑን ሊቃውንት ጉባኤ ገልጿል ስለሆነም ጉባኤው በተያዘለት መርሐ ግብር መሰረት የሚካሔድ ይሆናል።

ሊቃውንት ጉባኤ ያስተላለፈው ውሳኔ ደርሶናል እንደሚከተለው ይነበባል፦

ማሳሰቢያ
ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም.
የዝክረ ኒቅያ ጉባኤ የሚካሄድበት ቀን ማስተካከልን ይመለከታል።

የቅዱስ ሲኖዶስ መጋቢ የሆነው ሊቃውንት ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በተወሰነለት መሠረት፦ በአሁኑ ሰዓት ውይይትና ምክክር በሚያስፈልጋቸው የትውልድ ዐበይት ጥያቄዎች ላይ በመምከር ያለፈውን
ለማጽናት፣ የሚመጣውን ለማቅናት፥ ሃይማኖትና ቀኖናን ጠብቆ ለማስጠበቅ የሊቃውንት መሰባሰብ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ “ዝክረ ኒቅያ” በሚል
ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ ሊቃውንት ከጥር 26-29 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለማካሄድ ታቅዶ እንቅስቃሴሲደረግ ቆይቷል።

ሆኖም፦
1ኛ) ጉባኤው በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንት የሚታደሙበት እንደመሆኑ፥ በተለይ በጠረፉ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ
መምህራንን በበቂ ቊጥር ለማካተት እንዲቻል፥ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ፤

2ኛ) በጥር ወር በርካታ ሀገራዊ ክንውኖችና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት በየአካባቢው የሚካሄዱ በመሆናቸው የጉባኤው መካሄጃ ጊዜ እንዲስተ ካከል ከአንዳንድ አህጉረ ስብከት በተደጋጋሚ አስተያየት በመሰጠቱ፤

3ኛ) ጉባኤው ከዘመናት ቆይታ በኋላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድና በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ዙሪያ ጠቃሚ ውይይቶችን በማካሄድ፥

ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚጠቅም የውሳኔ ሐሳብና አስተያየት የሚያቀርብ፥ አልፎም የአቋም መግለጫ የሚያወጣ በመሆኑ፤የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ከመካሄዱ ጥቂት ቀደም ብሎ ከሚያዝያ 20-24ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲካሄድ በሊቃውንት ጉባኤ መወሰኑን በአክብሮትእየገለጸን፤ የአህጉረ ስብከት የሥራ ኀላፊዎች የተሳታፊዎች ልየታ መመሪያ እስከሚደርሳቸው ድረስ ለጉባኤው ይመጥናሉ የሚሏቸውን መምህራን በመለየት ዝግጅት እያደረጉ እንዲቆዩ አደራ እንላለን።

ሊቃውንት ጉባኤ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2025-02-01 10:51:232025-02-01 10:51:23የ”ዝክረ ኒቅያ ዓለም አቀፍ ጉባኤ” ከሚያዚያ 20-24 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ ሊቃውንት ጉባኤ አስታወቀ።
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የግብፅ  ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የግብፅ  ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top