ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡብ እና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ፣ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክርና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ አላማጣ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
ከሦስት ዓመታት በፊት የቋሚ ሲኖዶስ ተረኛ መሆናቸውን ተከትሎ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት የመጡት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በአዲስ አበባ ለመቆየት በመገደዳቸው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሳይሔዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል ጥንታዊ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ ሁኔታ ሰላማዊና ደማቅ በሆነ መልኩ እንዲከበር ሁሉም ወገን በኃላፊነት መንፈስ እንዲሠራ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አሳሰቡ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓልን በማስመልከት “ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ ሰላምን እሻ ተከተላትም” (መዝሙር ፴፬፥፲፫) የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኀይለ ቃል መነሻ በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት የጥምቀት በዓል ጥንታዊና ሃይማኖታዊ መሰረቱን በጠበቀ መልኩ ሰላማዊ በሆነና በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ በኃላፊነት መንፈስ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባው ገልጸዋል።
የብፁእ አቡነ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ ጉዞ በቤተ ክርስቲያን ሕግ እና ሥርዓት መሠረት የተፈቀደ ነው።
ብፁእ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኔዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገረ ስብከታቸው የጥምቀትን በዓል ለማክበር መጓዛቸው ይታወቃል። ጉዟቸውን በተመለከተ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተናፈሰ ያለው ወሬ እጅግ የተሳሳተ ሲሆን የብፁእነታቸው ሐዋርያዊ ጉዞ በቤተ ክርስቲያን ሕግ እና ሥርዓት መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነ እና በቅዱስ ፓትርያርኩ የተፈቀደ መሆኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
የ2016 ዓ.ም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት የቅዱስ ፓትርያርኩ የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ተከናወነ።
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ፣ አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
የሰላማችን ሰንደቅ ዓላማ የሆነው ወልድ ወይም ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ተወለደልን
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት፡፡
የቤተክርስቲያናችን የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ አባል ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ ታሠሩ ።
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የዕለት ችሎት ተከራርክሮ ከፍርድ ቤት ወጥቶ ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር ሜክሲኮ በሚገኘው ነዳጅ ማደያ ለመኪናው ነዳጅ በመቅዳት ላይ ሳለ ሲከታተሉት በነበሩ በመንግስት የጸጥታ አካላት ተወስዶ የታሠረ መሆኑ ታወቀ።
ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመሪ ምሥራቀ ጸሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተገኝተው የሕንፃ ግንባታው ሒደት ጎበኙ።
ታኅሣሥ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሓፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞ ጅንካ ፣ የአሪ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ሰላማ የምዕራብ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም መልአከ ምሕረት ዘካርያስ ሐዲስ የየካና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሪ ምሥራቀ ጸሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተገኝተው የሕንፃ ግንባታው ሒደት ጎብኝተው መንፈሳዊ አገልግሎት ሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በእስራኤል የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተመለሱ።
የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ለሚያስገነባው ባለ ዐስራ ሁለት ወለል ሕንጻ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በግራንድ ኤልያና ሆቴል አካሂዷል።
ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ባከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ለሚያስገነባው ባለ ዐስራ ሁለት ወለል ሕንጻ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በግራንድ ኤልያና ሆቴል አካሂዷል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከእስራኤል የቱሪዝም ሚንስትር ጋር ተወያዩ፤የእስራኤል ሙዝየምንም ጎበኙ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ አገልግሎት ቀጥለዋል።