ልማት በቤተ ክርስቲያን
ልዮ ዕትም መጽሔት
ይህ ”ልማት በቤተክርስቲያን“ የተሰኘ ልዮ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበ በአቡዳቢ ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያንበዓለ ጰራቅሊጦስ ተከበረ።
በዓለ ጰራቅሊጦስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በአቡዳቢ ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።
ወቅታዊ መልዕክት ለምዕመናን
የደብረ ኤልያስ ብሔረ ብፁዓን መልክዓ ሥላሴ አንድነት ገዳምን በተመለከተ በበርካታ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችና የመገናኛ አውታሮች ልዩ ልዩ ዘገባዎች እየተላለፉ ይገኛሉ።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን በተመለከተ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚዘዋወረው ዘገባ ከእውነት የራቀ ነው።
ሰሞኑን በአንዳንድ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን በማስመልከት የሚሰራጩት ዜናዎች ፍጹም ከእውነት የራቁና ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር የሚነዙ ሐሰተኛ ዘገባዎች ናቸው።
በባህርዳር የተገነባው ባለ ፮ ወለል ሁለ ገብ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተመረቀ።
የባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ገዳም ያስገነባው ባለ ስድስት ወለል ሁለ ገብ ሕንፃ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ግግቦት ፳ ቀን ፳ ፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ተመርቋል።
የግንቦት ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ ፲ ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።
ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት ፩ ቀን ፳፻ ፲ወ ፭ዓ.ም አስከ ግንቦት ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ድርስ በ ፲፰ አጀንዳዎች ዙሪያ የርክበ ካህናት ጉባኤውን ሲያካሒድ ከቆየ በኋላ ዛሬ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ ፭ዓ.ም ፲ ነጦቦችን የያዘ መግለጫ በማውጣት ጉባኤውን አጠናቋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በ፯ኛ ቀን ውሎው በአራት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ።
ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባካሄደው ውይይት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርቷን ለትውልዱ የታስተምርበት ተቋማት አንዱ መንፈሳዊ ኮሌጆች መሆነቸውን አውስቷል፡፡ እነዚህ ኮሌጆች ወጥ የሆነ ሕግ ሳይኖራቸው የቆየ ሲሆን በቅርቡም በሐዋሳ እና በወልቂጤ የተቋቋሙት ኮሌጆች ባቀረቡት መተዳደሪያ ደንብ መሠረት፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ውይይት አድርጎ ለሁሉም መንፈሳዊ ኮሌጆች የሚያገለግል ወጥ የሚሆን ሕግ አዘጋጅቶ ማጽደቁን ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡
የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት የሁለተኛው ቀን ውሎን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባባቢዋ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማብራሪያ ሰጡ።
ቅዱስ ሲኖዶስ በ2ኛ ቀን ውሎው የተከፋፈለ ሲኖዶስ እንደሌለ እና ከዚህ ሐሳብ ውጪ የሆነ አካል ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጪ የሆነ መሆኑን በመግለጽ መንግሥትን የሚያነጋግሩ ልዑካን ሰይሟል። በቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ያሉ አባቶችና አባላቱን በአካል የሚያነጋግሩ ብፁዓን አባቶች ተመርጠው ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር ሙሉ ቃል
የሰላም አለቃ፣የምሕረት አባት የሆነው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት የሆነችውን በዓለ ትንሣኤውን አክብረን ይህንን የረክበ ካህናት ቀኖናዊና ሲኖዶሳዊ ጉባኤ እንድናካሂድ ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ ለእሱ በማቅረብ፣እንኳን ደኅና መጣችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
በጠቅላይ ቤተክህነት እየተገነባ ያለው ዓለም አቀፍ ሁለገብ አዳራሽ የግንባታ ሥራው ፹፯ ፐርሰንት መድረሱ ተገለጸ።
በሥልጠናው መዝጊያ ላይ የተገኙት ብጹዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በህዝብ ግንኘነት አስፈላጊነትና ለቤተክርስቲያን ያለውን ፋይዳ በዝርዝር ገልጸው ቤተክርስቲያን በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ዘመኑን የዋጀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ የመድኃኔዓለም በዓልን በምስካየ ኀዙናን መድኃኔዓለም ገዳም አከበሩ
በሥልጠናው መዝጊያ ላይ የተገኙት ብጹዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በህዝብ ግንኘነት አስፈላጊነትና ለቤተክርስቲያን ያለውን ፋይዳ በዝርዝር ገልጸው ቤተክርስቲያን በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ዘመኑን የዋጀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።