የቦታው ስም ቀራንዮ ነው
የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ሕግና ደንብ የሚመራ “ፍኖተ ጽድቅ ብሮድካስት አገልግሎት” የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሊከፈት ነው።
ድርጅቱ የሚያቋቁመው ዘመናዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚተዳደርበት ደንብና የሚዲያ ሥራውን የሚያከናውንበት ኤዲቶሪያል ፓሊሲ የቤተ ክርስቲያናችንን ዶግማ፣ቀኖና፣ሕግና መመሪያን መሠረት ያደረገ ሆኖ መዘጋጀት ይችል ዘንድ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ከታዋቂ ሰባኪያን፣ከታላላቅ የአገራችን የቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደርጓል።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፍ/ደ/መዊዕ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅ/አርሴማ ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤትለሚያሳንጸው ሕንጻ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ እና ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ የፍ/ደ/መዊዕ ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ሰበካ ጉባኤ ለሚያሳንጸው ሕንጻ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።
ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደ.መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል መርሐ ግብር የተሳካ እንዲሆን ላደረገው አስተዋጽጾ ምጋና ተቸረ።
የቅዱስ ፓትርያርኩን ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም መመለስን አስመልክቶ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለቅዱስነታቸው ክብር በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀው መርሐ ግብር የተሳካና ውጤታማ መሆን ይችል ዘንድ የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታና የደብረ መድሐኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ሊቃውንትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ለመርሐ ግብሩ የሚመጥኑ ልዩልዩ ያሬዳዊ ዜማዎችን በማቅረብ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አድርገዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የአሜሪካ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰሜን አሜሪካ ሲያደርጉት የቆዩትን ሕክምና አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸውና ወደ ወንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።
ከነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ይሆናል።
የቦሌና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተሞች ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የ፳፻ ፲ወ፭ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አደረገ፤ በሥራ አፈጻጸም ውጤት ያስመዘገቡ አድባራትን ሸለመ።
ዛሬ በቦሌና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ በተደረገ የ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የአዲሱ ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በተደረገ ስብሰባ ላይ በክፍላተ ከተማው ሥር የሚሚገኙ አድባራትና ገዳማት በተለይም ውጤታማ የሥራ ክንውን ላደረጉት የሽልማት መርሐ ግብር ተከናውኗል።
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች የተተከሉ ሦስት አብያተክርስቲያናትን ባርከው ቅዳሴ ቤታቸውን አክበሩ በቢሻን ዋዩ ሐርቅ ለሚተከለው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኖሩ።
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላና የደቡብ ሱዳን፣ የቤኒሻንጉል አሶሳ፣ቄለም ወለጋ ቤጊ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጋምቤላ ሀገረስብከት መጃንግ ዞን መንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች ለሐዋርያዊ አገልግሎት በመጓዝ ሦስት አዳዲስ የተሰሩ አብያተክርስቲያናትን በመባረክ ቅዳሴ ቤታቸውን አክብረዋል።
በኒው ዮርክና አካባቢው የሚገኙ የአሀት ኦርቶዶክሳዊት (Oriental) ቤተክርስቲያን ብፁዓን አበው፣ ካህናትና ምእመናን በጋራ ለጸሎተ ቅዳሴ ተሰባሰቡ።
የአሀት ኦርቶዶክሳውያን አብያተክርስቲያናት ብፁዓን አባቶች ጉባኤ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን የጋራ የጸሎተ ቅዳሴ አገልግሎት መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም በዌስት ኦሬንጅ ኒውጀርሲ በሚገኘው ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አከናውነዋል።
ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለማኅሌት አገልግሎት ከምትጠቀምባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው የማኅሌተ ጽጌ መጽሐፍ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጎመ። ይህንን የአባ ጽጌ ድንግል ድርሰት የሆነው መጽሐፍ የተረጎሙት የፊንላንድ ሀገር ዜጋ የሆኑት እና ከሃምሳ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት ቆይታ ያደረጉት አቶ ኒሎ ሆንካነን ናቸው። ተርጓሚው መጽሐፉ ወደ ፊንላንድኛ ለመተርጎም ከ10 ዓመት በላይ ሲያጠኑ እንደቆዩና ዋና ምንጭ አድርገው የተጠቀሙት ደግሞ በ1919 ዓ.ም. በዶ/ር አዶልፍ ግሮህማን የተተረጎመውን የጀርመንኛ ቅጅ እንደሆነ ገልጸዋል።
የብፁዕ አቡነ ሰላማ ክቡር አስከረን ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጓዘ።
በሀሌሉያ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በትላንትናው እለት ከዚህዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ክቡር አስከሬናቸው ወደበመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸልተ ፍትሐት ሲደረግበት እንዲያድር እና በነገው እለት ቅዳሴ ከተቀደሰ በኋላ አስፈላጊው ሥርዓት ከተፈጸመለት በኋላ ሥርዓተ ቀብሩ እንዲፈጸም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጉዟል።