የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ባከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

December 13, 2023

የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ለሚያስገነባው ባለ ዐስራ ሁለት ወለል ሕንጻ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በግራንድ ኤልያና ሆቴል አካሂዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር)፣ የጅጅጋ ሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም(ዶ/ር)፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ እና የአዲስ አበባ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ኃ/ማርያም መድኅን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የሚገነባው አዲሱ ሕንጻ ማእከሉ ወጣት የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በሙሉ አቅሙ በማስተማር የቤተ ክርስቲያን እና የሀገር ተረካቢ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ እና በማእከሉ ለሚከናወኑ ልዩ ልዩ የሐዋርያዊ አገልግሎት፣ የሙያ አገልግሎት፣የሚዲያ ተደራሽነት እና ለቅዱሳት መካናት ተግባራት አቅም የሚፈጥር መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ለሁሉ ነገር መሠረት እና ለምንፈልገው ለውጥ የምርምር እና የትምህርት ተቋማት ያስፈልገናል ብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አክለውም የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ትልልቅ ተቋማትን ለማቋቋም የማንንም ርዳታ ሳንጠብቅ ዐሥር ሚልዮን የምንሆን ኦርቶዶክሳውያን በዓመት ውስጥ ባሉን የፆም ወቅቶች ብቻ ለቁርስ ወጪ የምናደርገውን ብናዋጣ ዓላማችንን ማሳካት እንችላለን ብለዋል፡፡

በመልዕክታቸው መጨረሻ ላይም ይህ የአዲስ አበባ ማእከል ሕንጻ የዚህ ስኬት አካል ስለሆነ ሁላችንም የድርሻችንን ብንወጣ በአንድ ዓመት ውስጥ መጨረስ እንችላለን በማለት ተናግረዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በበኩላቸው ይህ ዛሬ በአዲስ አበባ ማእከል እየተገነባ ያለው የወጣቶች ማእከል በአጠቃላይ ወጣቱ ትውልድ ስለ አገሩና ስለቤተ ክርስቲያኑ የሚመራመርበት፣ ዘመኑ ከሚያመጣቸው ፈተናዎች ተጠብቆ ለበጎ ነገር የሚነሳሳበት መሆኑን ተገንዝበን ምዕመናን ሁሉ ተረባርበን በአጭር ጊዜ ልናጠናቅቀው ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሰብሳቢው አክለውም ማኅበሩ ባለፉት 32 ዓመታት በሀገር ውስጥ እና በውጪ፣ በገጠርና በከተማ ውጤታማ ተግባራትን ማሳካት የቻለው በአባቶች ቡራኬ፣ በአባላቱ ጠንካራ ሥራ እና በምዕመናን ድጋፍ በመሆኑ ይህ ፕሮጀክት እንዲሳካ የሁሉም አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በዕለቱ በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ ከተገኙት ታዳሚዎች 7,500,000.00 (ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር) ቃል የተገባ ሲሆን ለዚህ በጎ ዓላማ ምዕመናን ሁሉ እንዲሳተፉ የሕንጻ ግንባታ ኮሚቴው ጥሪውን አቅርቧል፡፡
© M.K

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከእስራኤል የቱሪዝም ሚንስትር ጋር ተወያዩ፤የእስራኤል ሙዝየምንም ጎበኙ። Link to: ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከእስራኤል የቱሪዝም ሚንስትር ጋር ተወያዩ፤የእስራኤል ሙዝየምንም ጎበኙ። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ... Link to: ብፁዕ አቡነ አብርሃም በእስራኤል የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተመለሱ። Link to: ብፁዕ አቡነ አብርሃም በእስራኤል የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተመለሱ። ብፁዕ አቡነ አብርሃም በእስራኤል የነበራቸውን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top