የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በእስራኤል የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተመለሱ።

December 15, 2023

ታኅሣሥ ፭ቀን፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
————————-
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፥ የባህር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ በእስራኤል በነበራቸው የ፭ ቀናት ሐዋርያዊ አገልግሎት በሀገረ እስራኤል ከሚገኙ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም ኢትዮጵያውያን በዐበይት በዓላት ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ያለምንም መንገላታት ቪዛ በሚያገኙትበት ሁኔታና በሀገሪቱ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ገዳማት ዙሪያ ተነጋግረዋል። በተለይም በዴር ሱልጣን ገዳማችን በየጊዜው ስለሚፈጠረው ሁከትና ኢትዮጵያውያን በአልን በሰላም እንዳያከብሩ ስለሚደርስባቸው በደል አስረድተው የጥንት ይዞታችን ተከብሮ በዓልን በሰላም እንድናከብር ገንቢ ውይይት አድርገዋል።

በሌላ በኩል በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ከሚያገለግሉ መነኮሳት ጋር ገዳማቱ አንድነታቸው ተጠብቆ ሰላምና ፍቅር የነገሠበት አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያ ያስተላለፉ ሲሆን ፤ በሌሎች ጉዳዮች ደግሞ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። የኢትዮጵያ ገዳማትንና በገዳማቱ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ሊደረግ ስለሚገባው እገዛና ድጋፍም ከብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስና ከማኀበሩ ጋር ጥልቅ ውይይት አድርገዋል።

ብፁዕነታቸው በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቅዱሳት መካናትን የተሳለሙ ሲሆን ፤ በሀገረ እስራኤል የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ሲመለሱ በቴልአቪቭ ቤንጎርዮን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስና በገዳማቱ በሚያገለግሉ አበው መነኮሳት ሽኝት ተደርጐላቸዋል።© EOTC TV

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ባከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ Link to: ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ባከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ባከናወነው... Link to: ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመሪ ምሥራቀ ጸሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተገኝተው የሕንፃ ግንባታው ሒደት ጎበኙ። Link to: ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመሪ ምሥራቀ ጸሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተገኝተው የሕንፃ ግንባታው ሒደት ጎበኙ። ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመሪ ምሥራቀ ጸሐይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top