ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በባህርዳር ሀገረ ስብከት የሚከናወኑ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ፣ወደፊት በሚሰሩ የልማት ሥራዎች ዙሪያም የሥራ መመሪያ ሰጡ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሚያዝ ፰ -፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ያስጀነመሯቸውን ሕንፃ አብያተ ክርስቲያናትና ልዩልዩፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል ። በፕሮጀክቶቹ ዙሪናም ድጋፍና ክትትልም አድርገዋል፣ ከገዳማትና አድባራት አስተዳደር ክፍሎች ጋርም ውይይት አካሂደው የሥራ መመሪያና ወደፊት መአናወን በሚገባቸው ሥራዎች ዙሪያም አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በጀርመን ከሙንስተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጋር ውይይት አደረጉ።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መጋቢት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ ም በጀርመን ሙንስትር ከተማ በመገኘት ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሙንስተርና አካባቢ ጳጳስ ከኾኑት ዶክተር ፊልክስ ጌን ጋር ውይይት ውይይት ማድረጋቸውን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ገልጿል።
ቅዱስ ሲኖዶስ መጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ምልአተ ጉባኤ እንዲካሄድ ጥሪ ተላለፈ
በህገ ወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በአምስት ቀናት ውስጥ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት መገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላለፈ።
በምሥራቅ አውሮፖ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው ከተማ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የምሥራቅ ጎጃም፣ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተባርኮ አገልግሎት ጀምሯል ።
የመምህር የኔታ ሐረገወይን ምሕረቱ የሽኝት መርሐ ግብር
የመምህር የኔታ ሐረገወይን ምሕረቱ የሽኝት መርሐ ግብር ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት የምምሪያ ኃላፊዎች የመንግስት ባለሥልጣናት፣የባቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተፈጸመ።
ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ የሕይወት ታሪክ
ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ በወሎ ክፍለ ሀገር ሰገራት (ኩታበር ወደ ግሸን መሔጃ) ከወላጅ አባታቸው ከአለቃ ምሕረቱ ካሣ ከእናታቸወ ወ/ሮ አበቡ ወልደ ጻድቅ በየካቲት 16 ቀን 1916 ዓ.ም ተወለዱ። የፊደልና ንባብ ትምህርት የጀመሩት በእናታቸው ሀገር በቦሩ ሥላሴ ነው።
ፍርድ ቤቱ የሕገወጥ ቡድኑን መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከጠየቀችው ዘጠና ቀናት ውስጥ የ፵፭ ቀናት የእግድ ትዕዛዝ ወሰነ።
የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብሩ በብፁዓን አባቶች የሚመራ አምስት አባላት ያሉት ዐቢይ ኮሚቴ ተመደበ፤
. . . በሦስት ብፁዓን አባቶች እና በሁለት የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ ዐቢይ ኮሚቴ እንዲዋቀርና ወደ ሥራ እንዲገባ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ሰጥቷል።
የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/መገናኛ ብዙሃን ሥርጭት ድርጅትና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በሰው ሃይል እንዲጠናከሩ ወሰነ።
. . . በቀጣይ ጊዜ በሁለቱ ተቋማት በጥምረትና በተናጠል መሰራት ያለባቸው ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ጉባኤው ያመላከተ ሲሆን በተለይም መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ወቅታዊ ምላሽ የመስጠትና በየዕለቱ የዜና ሽፋን የመስጠት ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፬ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፬ኛ ዓመታ መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስ ስላሴ ካቴድራል ብፁዕአን ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውተ ቤተክርስቲያን ወዳጆቻቸው እና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።